2 ነገሥት 25:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተማዪቱም እስከ ንጉሥ ሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት ዐሥራ አንደኛ ዓመት ድረስ እንዲሁ እንደ ተከበበች ቈየች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከበባውም እስከ ሴዴቅያስ ዐሥራ አንደኛ ዓመት ዘመነ መንግሥት ድረስ ቆየ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከበባውም እስከ ሴዴቅያስ ዐሥራ አንደኛ ዓመት ዘመነ መንግሥት ድረስ ቈየ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከተማዪቱም እስከ ንጉሡ እስከ ሴዴቅያስ ዐሥራ አንደኛው ዓመተ መንግሥት እስከ አራተኛው ወር እስከ ዘጠነኛው ቀን ድረስ ተከብባ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከተማይቱም እስከ ንጉሡ እስከ ሴዴቅያስ እስከ ዐሥራ አንደኛው ዓመት ድረስ ተከብባ ነበር። |
በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር፣ ከወሩም በዐሥረኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር መላ ሰራዊቱን ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ዘመተ፤ ከከተማዪቱ ቅጥር ውጭ ሰፈረ፤ ዙሪያውንም በሙሉ በዕርድ ከበባት።
የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በዐሥረኛው ዓመት፣ ይኸውም በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር ዐሥራ ስምንተኛ ዘመነ መንግሥት፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፤
የምትታመንባቸውን ታላላቅ የተመሸጉ ቅጥሮች እስኪወድቁ ድረስ በመላው አገርህ ያሉትን ከተሞችህን ሁሉ ይከብባል፤ አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ያሉትን ከተሞች በሙሉ ይወርራቸዋል።