Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ነገሥት 25:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር፣ ከወሩም በዐሥረኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር መላ ሰራዊቱን ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ዘመተ፤ ከከተማዪቱ ቅጥር ውጭ ሰፈረ፤ ዙሪያውንም በሙሉ በዕርድ ከበባት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ከዚህ በኋላ ናቡከደነፆር መላው ሠራዊቱን አስከትቶ ሴዴቅያስ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት፥ ዐሥረኛው ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን በኢየሩሳሌም ላይ ዘመተ፤ ወታደሮቹ ከከተማይቱ ውጪ ሰፍረው ዙሪያውን የሚከብብ የዐፈር ቁልል ሠሩ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከዚህ በኋላ ናቡከደነፆር መላው ሠራዊቱን አስከትቶ ሴዴቅያስ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት፥ ዐሥረኛው ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን በኢየሩሳሌም ላይ ዘመተ፤ ወታደሮቹ ከከተማይቱ ውጪ ሰፍረው ዙሪያውን የሚከብብ የዐፈር ቊልል ሠሩ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ሴዴ​ቅ​ያ​ስም በነ​ገሠ በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመት በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከሠ​ራ​ዊቱ ሁሉ ጋር ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጥቶ ሰፈ​ረ​ባት፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ዕርድ ሠራ​ባት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ሴዴቅያስም በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር ከወሩም በዐሥረኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ከበቡአት፤ በዙሪያዋም ዕርድ ሠሩባት።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 25:1
33 Referencias Cruzadas  

በዙሪያሽ እሰፍራለሁ፤ በቅጥር እከብብሻለሁ፤ የከበባ ዐምባም ሠርቼ አስጨንቅሻለሁ።


እግዚአብሔር የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ በናቡከደነፆር እጅ ተማርከው እንዲወሰዱ ባደረገ ጊዜ ኢዮሴዴቅም ዐብሮ ተማርኮ ሄደ።


“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘የነገሥታት ንጉሥ የሆነውን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን ከፈረሶችና ከሠረገሎች ጋራ፣ ከፈረሰኞችና ከታላቅ ሰራዊትም ጋራ ከሰሜን በጢሮስ ላይ አመጣለሁ።


“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላን፣ አድቅቆ ፈጨን፤ እንደ ባዶ ማድጋ አደረገን፤ እንደ ዘንዶ ዋጠን፣ እንደ ጣፋጭ በልቶን ሆዱን ሞላ፤ በኋላም አንቅሮ ተፋን፤


እንዲህም በላቸው፤ ‘የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ አገልጋዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እንዲመጣ አደርጋለሁ፤ ዙፋኑንም እዚህ በቀበርኋቸው ድንጋዮች ላይ እዘረጋለሁ፤ የንጉሥ ድንኳኑንም በላያቸው ይተክላል።


ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ እነሆ፤ ይህችን ከተማ ለባቢሎናውያንና ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር አሳልፌ እሰጣታለሁ፤ እርሱም ይይዛታል።


“እነሆ፤ ከተማዪቱን ለመያዝ የዐፈር ድልድል በዙሪያዋ ተሠርቷል፤ ከሰይፍ፣ ከራብና ከቸነፈር የተነሣ ከተማዪቱን ለሚወጓት ለባቢሎናውያን ዐልፋ ልትሰጥ ነው፤ እንደምታየውም የተናገርኸው እየተፈጸመ ነው።


“ ‘ “ነገር ግን ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር የማይገዛ፣ ዐንገቱንም ከቀንበሩ በታች ዝቅ የማያደርግ ማንኛውንም ሕዝብ ወይም መንግሥት በእጁ እስከማጠፋው ድረስ በሰይፍና በራብ፣ በመቅሠፍትም እቀጣዋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤


በዚያ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ የናቡከደነፆር ጦር አለቆች ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ መጥተው ከበቧት፤


በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ምድሪቱን ወረረ፤ ኢዮአቄምም ሦስት ዓመት ገበረለት፤ ከዚያ በኋላ ግን ሐሳቡን ለውጦ በናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ።


ከተማዪቱም እስከ ንጉሥ ሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት ዐሥራ አንደኛ ዓመት ድረስ እንዲሁ እንደ ተከበበች ቈየች።


ሰብል እንደሚጠብቁ ሰዎች ይከቧታል፤ በእኔ ላይ ዐምፃለችና፤’ ” ይላል እግዚአብሔር።


እረኞች መንጎቻቸውን ይዘው ይመጡባታል፤ ድንኳናቸውን በዙሪያዋ ይተክላሉ፤ እያንዳንዳቸውም በየአቅጣጫቸው መንጋቸውን ያሰማራሉ።


“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሊወጋን ስለ ሆነ፣ እባክህን ፈጥነህ፣ እግዚአብሔርን ጠይቅልን፤ ምናልባት ንጉሡ ከእኛ ይመለስ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ቀድሞው ታምራት ያደርግልን ይሆናል” ብለው ነበር።


የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በዐሥረኛው ዓመት፣ ይኸውም በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር ዐሥራ ስምንተኛ ዘመነ መንግሥት፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፤


“እስራኤል አንበሶች ያሳደዱት፣ የተበተነ መንጋ ነው፤ መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ፣ ቦጫጭቆ በላው፤ በኋላም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር፣ ዐጥንቱን ቈረጣጠመው።”


“እንግዲህ፣ የሰው ልጅ ሆይ፤ ትንቢት ተናገር፤ በእጅህም አጨብጭብ፤ ሰይፉ ሁለት ጊዜ፣ ሦስት ጊዜም ይምታ፤ በእጅጉ የሚገድል፣ ለግድያ የሚሆን፣ በየአቅጣጫውም የሚከባቸው ሰይፍ ነው።


በተሰደድን በሃያ ዐምስተኛው ዓመት፣ በዓመቱ መጀመሪያ፣ በዐሥረኛው ቀን፣ ከተማዪቱ በወደቀች በዐሥራ አራተኛው ዓመት፣ በዚያው ዕለት የእግዚአብሔር እጅ በላዬ ነበር፤ እርሱም ወደዚያ ወሰደኝ።


የምትታመንባቸውን ታላላቅ የተመሸጉ ቅጥሮች እስኪወድቁ ድረስ በመላው አገርህ ያሉትን ከተሞችህን ሁሉ ይከብባል፤ አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ያሉትን ከተሞች በሙሉ ይወርራቸዋል።


የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በነገሠ በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት፣ በዐምስተኛው ወር ከወሩም በሰባተኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ባለሟል የክብር ዘበኞች አዛዥ የነበረው ናቡዘረዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።


ሴዴቅያስ ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ አንድ ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ።


በዚያ ጊዜም የባቢሎን ንጉሥ ሰራዊት ኢየሩሳሌምን ከብቦ ነበር፤ ነቢዩ ኤርምያስም በይሁዳ ንጉሥ ቤተ መንግሥት በዘብ ጠባቂዎች አደባባይ ተዘግቶበት ነበር።


ሴዴቅያስ ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ አንድ ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ የእናቱም ስም አሚጣል ነበረ፣ እርሷም የልብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።


የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የአራተኛው፣ የአምስተኛው፣ የሰባተኛውና የዐሥረኛው ወር ጾሞች ለይሁዳ ቤት የደስታ፣ የተድላና የሐሤት በዓላት ይሆናሉ፤ ስለዚህ እውነትንና ሰላምን ውደዱ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios