2 ነገሥት 16:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአካዝ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ተግባርና የፈጸመውም ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሥ አካዝ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ አካዝ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀረውም አካዝ ያደረገው ነገር እነሆ፥ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀረውም አካዝ ያደረገው ነገር በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? |
የአሦርንም ንጉሥ ለማስደሰት ሲል፣ በዕለተ ሰንበት ንጉሣዊ ዙፋን እንዲዘረጋበት በቤተ መቅደሱ ውስጥ የተሠራውን ከፍ ያለ ስፍራና ነገሥታቱ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚገቡበትን በውጭ ያለውን መግቢያ አነሣ።
በአካዝ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ተግባርና አካሄዱ ሁሉ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፏል።