2 ነገሥት 14:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አስከሬኑን በፈረስ ጭነው አመጡ። እንደ አባቶቹም ሁሉ በዳዊት ከተማ፣ በኢየሩሳሌም ተቀበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሬሳውም በፈረስ ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘውም የነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሬሳውም በፈረስ ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘውም የነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በድኑንም በፈረስ ጭነው አመጡት፤ በኢየሩሳሌምም በዳዊት ከተማ ከአባቶቹ ጋር ቀበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፈረስም ጭነው አመጡት፤ በኢየሩሳሌምም በዳዊት ከተማ ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ። |
ገዳዮቹ ሹማምትም የሰምዓት ልጅ ዮዛካርና የሾሜር ልጅ ዮዛባት ነበሩ። እርሱም ሞተ፤ እንደ አባቶቹም ሁሉ በዳዊት ከተማ ተቀበረ። ልጁ አሜስያስም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
ኢዮራም ሲነግሥ ዕድሜው ሠላሳ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ስምንት ዓመት ገዛ። በሞተ ጊዜም ማንም አላዘነለትም፤ በዳዊት ከተማ እንጂ በነገሥታቱ መቃብር አልቀበሩትም።
ዖዝያንም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ። ሕዝቡም “ለምጽ አለበት” ብለው የነገሥታቱ በሆነው መቃብር አጠገብ ባለው ቦታ ቀበሩት፤ ልጁም ኢዮአታም በምትኩ ነገሠ።