ስለዚህ የቤተ መንግሥቱ አዛዥ፣ የከተማዪቱ ገዥ፣ ሽማግሌዎችና የልጆቹ ሞግዚቶች፣ “እኛ የአንተው አገልጋዮች ነን፤ ትእዛዝህን ሁሉ እንፈጽማለን፤ እኛ ማንንም አናነግሥም፤ ደስ የሚያሰኝህን ሁሉ አንተው አድርግ” በማለት ይህን መልእክት ለኢዩ ላኩ።
2 ነገሥት 10:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢዩ፣ “እንግዲህ የእኔ ወገን ከሆናችሁና ከታዘዛችሁኝ የጌታችሁን ልጆች ራስ ቈርጣችሁ ነገ በዚህ ሰዓት ይዛችሁልኝ ወደ ኢይዝራኤል እንድትመጡ” ሲል ደግሞ ጻፈላቸው። በዚህም ጊዜ ሰባው የንጉሡ ልጆች በከተማዪቱ ውስጥ ታዋቂ በሆኑ አሳዳጊዎቻቸው ዘንድ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዩም “እናንተ ከእኔ ጋር ከተባበራችሁና ትእዛዜንም ለመፈጸም ዝግጁዎች ከሆናችሁ፥ ነገ በዚህ ጊዜ የንጉሥ አክዓብን ዘሮች ሁሉ ራሶቻቸውን ቆርጣችሁ ይዛችሁልኝ ኑ” ሲል ሌላ ደብዳቤ ጻፈላቸው። ሰባው የንጉሥ አክዓብ ተወላጆች በሰማርያ አሳዳጊዎቻቸው በሆኑ በታወቁ የአገር ሽማግሌዎች ጥበቃ ሥር ነበሩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዩም “እናንተ ከእኔ ጋር ከተባበራችሁና ትእዛዜንም ለመፈጸም ዝግጁዎች ከሆናችሁ፥ ነገ በዚህ ጊዜ የንጉሥ አክዓብን ዘሮች ሁሉ ራሶቻቸውን ቈርጣችሁ ይዛችሁልኝ ኑ” ሲል ሌላ ደብዳቤ ጻፈላቸው። ሰባው የንጉሥ አክዓብ ተወላጆች በሰማርያ አሳዳጊዎቻቸው በሆኑ በታወቁ የአገር ሽማግሌዎች ጥበቃ ሥር ነበሩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ኢዩ፥ “ወገኖቼስ ከሆናችሁ፥ ነገሬንም ከሰማችሁ የጌታችሁን ልጆች ራስ ቍረጡ፤ ነገም በዚህ ሰዓት ወደ ኢይዝራኤል ወደ እኔ ይዛችሁ ኑ” ብሎ ሁለተኛ ደብዳቤ ጻፈላቸው። የንጉሡም ልጆች ሰባው ሰዎች በሚያሳድጓቸው በከተማዪቱ ታላላቆች ዘንድ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለተኛም “ወገኖቼስ እንደ ሆናችሁ፥ ነገሬንም ከሰማችሁ፥ የጌታችሁን ልጆች ራሶች ቍረጡ፤ ነገም በዚህ ሰዓት ወደ ኢይዝራኤል ወደ እኔ ይዛችሁ ኑ፤” ብሎ ደብዳቤ ጻፈላቸው። የንጉሡም ልጆች ሰባው ሰዎች በሚያሳድጓቸው በከተማይቱ ታላላቆች ዘንድ ነበሩ። |
ስለዚህ የቤተ መንግሥቱ አዛዥ፣ የከተማዪቱ ገዥ፣ ሽማግሌዎችና የልጆቹ ሞግዚቶች፣ “እኛ የአንተው አገልጋዮች ነን፤ ትእዛዝህን ሁሉ እንፈጽማለን፤ እኛ ማንንም አናነግሥም፤ ደስ የሚያሰኝህን ሁሉ አንተው አድርግ” በማለት ይህን መልእክት ለኢዩ ላኩ።
ደብዳቤውም በደረሳቸው ጊዜ፣ ሰዎቹ ሰባውን ልዑላን በሙሉ ወስደው ገደሏቸው። ራሳቸውንም በቅርጫት አድርገው ኢዩ ዘንድ ወደ ኢይዝራኤል ላኩ።
በማግስቱም ጧት ኢዩ ወጥቶ በሕዝቡ ሁሉ ፊት በመቆም እንዲህ አለ፤ “እናንተ ንጹሓን ናችሁ፤ ጌታዬን ያሤርሁበትና የገደልሁት እኔ ነኝ። እነዚህን ሁሉ ግን የፈጃቸው ማን ነው?
ቀና ብሎ ወደ መስኮቱ ተመለከተና፣ “ማነህ አንተ? ማነው የሚተባበረኝ” ሲል ጮኾ ተጣራ። ሁለት ሦስት ጃንደረቦችም ቍልቍል ወደ እርሱ ተመለከቱ፤
እግዚአብሔር ሙሴን፣ “አስፈሪው የእግዚአብሔር ቍጣ ከእስራኤል እንዲመለስ የሕዝቡን አለቆች ሁሉ ወስደህ ግደልና በጠራራ ፀሓይ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ስቀላቸው” አለው።
አትስገድላቸው ወይም አታምልካቸውም፤ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፣ የሚጠሉኝን ስለ አባቶቻቸው ኀጢአት እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ ልጆቻቸውን የምቀጣ ቀናተኛ አምላክ ነኝና።