2 ዮሐንስ 1:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ፍቅር፣ በትእዛዞቹ መሠረት እንመላለስ ዘንድ ነው። ትእዛዙም ከመጀመሪያ እንደ ሰማችሁት በፍቅር እንድትኖሩ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍቅር ይህ ነው፥ እርሱም በትእዛዛቱ መመላለስ ነው፤ ትእዛዙ ይህ ነው፥ ከመጀመሪያ ጀምሮ እንደ ሰማችሁት፥ በእርሱ ተመላለሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እውነተኛ ፍቅር ማለት የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መፈጸም ነው። ይህም ትእዛዝ በመጀመሪያ እንደ ሰማችሁት “በፍቅር ኑሩ” የሚል ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ትእዛዛቱም እንሄድ ዘንድ ይህ ፍቅር ነው፤ ከመጀመሪያ እንደ ሰማችሁ፥ በእርስዋ ትሄዱ ዘንድ ትእዛዙ ይህች ናት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ትእዛዛቱም እንሄድ ዘንድ ይህ ፍቅር ነው፤ ከመጀመሪያ እንደ ሰማችሁ፥ በእርስዋ ትሄዱ ዘንድ ትእዛዙ ይህች ናት። |
ወዳጆች ሆይ፤ የምጽፍላችሁ፣ ከመጀመሪያ የነበራችሁን የቈየውን ትእዛዝ እንጂ አዲስ ትእዛዝ አይደለም፤ የቈየው ትእዛዝ የሰማችሁት ቃል ነው።
አሁንም እመቤት ሆይ፤ እለምንሻለሁ፤ ከመጀመሪያ የነበረችውን እንጂ አዲስ ትእዛዝ አልጽፍልሽም፤ ይኸውም እርስ በርሳችን እንዋደድ ዘንድ ነው።