Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዮሐንስ 1:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ፍቅር ይህ ነው፥ እርሱም በትእዛዛቱ መመላለስ ነው፤ ትእዛዙ ይህ ነው፥ ከመጀመሪያ ጀምሮ እንደ ሰማችሁት፥ በእርሱ ተመላለሱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ይህም ፍቅር፣ በትእዛዞቹ መሠረት እንመላለስ ዘንድ ነው። ትእዛዙም ከመጀመሪያ እንደ ሰማችሁት በፍቅር እንድትኖሩ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እውነተኛ ፍቅር ማለት የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መፈጸም ነው። ይህም ትእዛዝ በመጀመሪያ እንደ ሰማችሁት “በፍቅር ኑሩ” የሚል ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እንደ ትእዛዛቱም እንሄድ ዘንድ ይህ ፍቅር ነው፤ ከመጀመሪያ እንደ ሰማችሁ፥ በእርስዋ ትሄዱ ዘንድ ትእዛዙ ይህች ናት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እንደ ትእዛዛቱም እንሄድ ዘንድ ይህ ፍቅር ነው፤ ከመጀመሪያ እንደ ሰማችሁ፥ በእርስዋ ትሄዱ ዘንድ ትእዛዙ ይህች ናት።

Ver Capítulo Copiar




2 ዮሐንስ 1:6
14 Referencias Cruzadas  

ትእዛዛቱን እንድንጠብቅ፥ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።


ከመጀመሪያ የሰማችሁት በእናንተ ውስጥ ይኑር። ከመጀመሪያ የሰማችሁት በእናንተ ውስጥ ከኖረ፥ እናንተም በወልድና በአብ ትኖራላችሁ።


ቃሉን የሚጠብቅ ግን በእውነት የእግዚአብሔርን ፍቅር በእርሱ ፍጹም ሆኗል። በእርሱ እንዳለን በዚህ እናውቃለን።


እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምኖር፥ ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።


“የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ።


እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ።


ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትንም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”


የምንጠይቀውን እንደሚሰማን ካወቅን፥ የጠየቅነውን እንደ ተቀበልን እናውቃለን።


አሁንም እመቤት ሆይ! አዲስን ትእዛዝ አልጽፍልሽም ነገር ግን ከመጀመሪያ ጀምሮ የነበረውን ነው፥ ይህም እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ እለምንሻለሁ።


አምላካችሁን ጌታን ተከተሉት፤ ፍሩት፤ ትእዛዞቹንም ጠብቁ፤ ታዘዙት፤ አገልግሉት፤ ከእርሱም ጋር ተጣበቁ።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን፤ በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን።


ወዳጆቼ ሆይ፥ አዲስ ትእዛዝ አልጽፍላችሁም፤ ነገር ግን ከመጀመሪያ የነበራችሁ አሮጌ ትእዛዝ ነው እንጂ፤ አሮጌውም ቃል የሰማችሁት ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios