ከዚህም በቀር ለአምላኬ ቤት ካለኝ ፍቅር የተነሣ፣ ለዚህ ለተቀደሰ ቤት ከዚህ በፊት ከሰጠሁት በተጨማሪ፣ ለዚሁ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የግል ሀብቴ የሆነውን ወርቅና ብር እሰጣለሁ፤
1 ሳሙኤል 9:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሦስት ቀን በፊት ስለ ጠፉብህ አህዮች አትጨነቅ፤ ተገኝተዋልና። የእስራኤል ምኞት ሁሉ ያዘነበለው ወደ አንተና ወደ አባትህ ቤተ ሰብ ሁሉ አይደለምን?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተገኝተዋልና፥ ከሦስት ቀን በፊት ስለ ጠፉብህ አህዮች አትጨነቅ። የእስራኤል ምኞት ሁሉ ያዘነበለው ወደ ማን ነው? ወደ አንተና ወደ አባትህ ቤተሰብ ሁሉ አይደለምን?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሦስት ቀን በፊት የጠፉት አህዮችህ ተገኝተዋልና ስለ እነርሱ አትጨነቅ፤ ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ ምኞት ማንን ለማግኘት ይመስልሃል? እነርሱ የሚፈልጉት አንተንና የአባትህን ቤተሰብ አይደለምን?” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሦስት ቀንም በፊት የጠፉ አህዮችህ ተገኝተዋልና ልብህን አታስጨንቀው። የእስራኤል መልካም ምኞት ለማን ነው? ለአንተና ለአባትህ ቤት አይደለምን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሦስት ቀንም በፊት የጠፉ አህዮችህ ተገኝተዋልና ልብህን አትጣልባቸው። የእስራኤልም ምኞት ለማን ነው? ለአንተና ለአባትህ ቤት አይደለምን? አለው። |
ከዚህም በቀር ለአምላኬ ቤት ካለኝ ፍቅር የተነሣ፣ ለዚህ ለተቀደሰ ቤት ከዚህ በፊት ከሰጠሁት በተጨማሪ፣ ለዚሁ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የግል ሀብቴ የሆነውን ወርቅና ብር እሰጣለሁ፤
ለመሞትም በምታጣጥርበት ጊዜ፣ በአጠገቧ የነበሩት ሴቶች፣ “አይዞሽ፤ ወንድ ልጅ ወልደሻልና በርቺ” አሏት። እርሷ ግን መልስ አልሰጠችም፤ ልብ ብላም አላዳመጠችም።
እነርሱም፣ “አንተ አርጅተሃል፤ ልጆችህ ያንተን ፈለግ አይከተሉም፤ ስለዚህ ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት ሁሉ የሚመራን ንጉሥ አንግሥልን” አሉት።
ሳሙኤልም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ባለራእዩ እኔ ነኝ፤ ዛሬ ከእኔ ጋራ ስለምትበሉ ከፊቴ ቀድማችሁ ወደ ማምለኪያው ኰረብታ ውጡ፤ ነገ ጧት አሰናብትሃለሁ፤ በልብህ ያለውንም እነግርሃለሁ።
በዚያም ጊዜ የሳኦል አባት የቂስ አህዮች ጠፍተው ነበር፤ ቂስም ልጁን ሳኦልን፣ “ከአገልጋዮቹ መካከል አንዱን ይዘህ ሂድና አህዮቹን ፈልግ” አለው።