Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ሳሙኤል 9:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በዚያም ጊዜ የሳኦል አባት የቂስ አህዮች ጠፍተው ነበር፤ ቂስም ልጁን ሳኦልን፣ “ከአገልጋዮቹ መካከል አንዱን ይዘህ ሂድና አህዮቹን ፈልግ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በዚያም ጊዜ የሳኦል አባት የቂስ አህዮች ጠፍተው ነበር፤ ቂስም ልጁን ሳኦልን፥ “ከአገልጋዮቹ መካከል አንዱን ይዘህ ሂድና አህዮቹን ፈልግ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የሳኦል አባት ቂስ፥ አህዮቹ ጠፍተውበት ነበር፤ ስለዚህም ልጁን ሳኦልን “ከአገልጋዮች አንዱን ይዘህ ሂድና የጠፉትን አህዮች ፈልግ” ብሎ አዘዘው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የሳ​ኦ​ልም አባት የቂስ አህ​ዮች ጠፍ​ተው ነበር፤ ቂስም ልጁን ሳኦ​ልን፥ “ከብ​ላ​ቴ​ኖቹ አን​ዱን ወስ​ደህ ተነ​ሡና ሄዳ​ችሁ አህ​ዮ​ችን ፈልጉ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የሳኦልም አባት የቂስ አህዮች ጠፍተው ነበር፥ ቂስም ልጁን ሳኦልን፦ ከብላቴኖቹ አንዱን ወስደህ ተነሣ፥ አህዮችንም ለመሻት ሂድ አለው።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 9:3
7 Referencias Cruzadas  

ኢያዕር በሠላሳ አህዮች የሚጋልቡ ሠላሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ልጆቹም እስከ ዛሬ ድረስ የኢያዕር መንደሮች ተብለው የሚጠሩ ሠላሳ ከተሞች በገለዓድ ምድር ነበሯቸው።


“እናንተ በነጫጭ አህዮች የምትጋልቡ፣ በባለ ግላስ ኮርቻ ላይ የምትቀመጡ፣ በመንገድ ላይ የምትጓዙ፣ በውሃ ምንጮች ዙሪያ ያለውን፣


በዚህ ጊዜ የሳኦል አጎት እርሱንና አገልጋዩን፣ “የት ነበራችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። እርሱም፣ “አህዮቹን ፍለጋ ሄደን ነበር፤ እንደማይገኙ በተረዳን ጊዜ ግን ወደ ሳሙኤል ሄድን” አለው።


ዛሬ ከእኔ ተለይተህ ስትሄድ፣ በብንያም ወሰን ላይ በምትገኘው ጼልጻህ በተባለች ስፍራ በራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች ታገኛለህ። እነርሱም፣ ‘የምትፈልጋቸው አህዮች ተገኝተዋል፤ አሁን አባትህ ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ፣ “ስለ ልጄ ምን ባደርግ ይሻለኛል?” እያለ በመጨነቅ ላይ ነው’ ይሉሃል።


ቂስም ከእስራኤል ልጆች መካከል በመልከ ቀናነቱ ተወዳዳሪ የማይገኝለት፣ ቁመቱም ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ ከትከሻው በላይ ዘለግ ያለ፣ ሳኦል የተባለ ወጣት ልጅ ነበረው።


ከሦስት ቀን በፊት ስለ ጠፉብህ አህዮች አትጨነቅ፤ ተገኝተዋልና። የእስራኤል ምኞት ሁሉ ያዘነበለው ወደ አንተና ወደ አባትህ ቤተ ሰብ ሁሉ አይደለምን?”


ስለዚህ በኰረብታማው በኤፍሬም አገርና በሻሊሻ አካባቢ ባለው ስፍራ ሁሉ ተዘዋወረ፤ ሆኖም አህዮቹን አላገኙም። ወደ ሻዕሊምም ግዛት ዘልቀው ገቡ፤ አህዮቹ ግን በዚያም አልነበሩም። እንዲሁም በብንያም ግዛት በኩል ዐለፈ፤ ሆኖም አላገኟቸውም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos