የፍልስጥኤም አዛዦችም፣ “እነዚህ ዕብራውያን እዚህ ምን እያደረጉ ነው?” ብለው ጠየቁ። አንኩስም፣ “ይህ የእስራኤል ንጉሥ የሳኦል አገልጋይ የነበረው ዳዊት አይደለምን? ከእኔ ጋራ መኖር ከጀመረ እነሆ ዓመት ዐለፈው፤ እኔን ከተጠጋበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ምንም በደል አላገኘሁበትም” አላቸው።
1 ሳሙኤል 4:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍልስጥኤማውያንም ይህን ታላቅ ጩኸት ሲሰሙ፣ “በዕብራውያን ሰፈር የምንሰማው ይህ ሁሉ ጩኸት ምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁ። የእግዚአብሔር ታቦት ወደ ሰፈር መምጣቱን በተረዱ ጊዜ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍልስጥኤማውያንም ይህን ታላቅ የሆታ ድምፅ ሲሰሙ፥ “በዕብራውያን ሰፈር የምንሰማው ይህ ሁሉ የሆታ ድምፅ ምንድነው?” ሲሉ ጠየቁ። የጌታም ታቦት ወደ ሰፈር መምጣቱን በተረዱ ጊዜ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍልስጥኤማውያንም ያንን የእልልታ ድምፅ ሰምተው “በዕብራውያን ሰፈር የምንሰማው ይህ ታላቅ የእልልታ ድምፅ ምን ይሆን?” ተባባሉ፤ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ዕብራውያን ሰፈር መምጣቱንም ባወቁ ጊዜ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍልስጥኤማውያንም የእልልታውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ “በዕብራውያን ሰፈር ያለው ይህ ታላቅ የእልልታ ድምፅ ምንድን ነው?” አሉ። የእግዚአብሔርም ታቦት ወደ ሰፈሩ እንደ ደረሰች አስተዋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍልስጥኤማውያንም የእልልታውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፦ በዕብራውያን ሰፈር ያለው ይህ ታላቅ የእልልታ ድምፅ ምንድር ነው? አሉ። የእግዚአብሔርም ታቦት ወደ ሰፈሩ እንደገባ አስተዋሉ። |
የፍልስጥኤም አዛዦችም፣ “እነዚህ ዕብራውያን እዚህ ምን እያደረጉ ነው?” ብለው ጠየቁ። አንኩስም፣ “ይህ የእስራኤል ንጉሥ የሳኦል አገልጋይ የነበረው ዳዊት አይደለምን? ከእኔ ጋራ መኖር ከጀመረ እነሆ ዓመት ዐለፈው፤ እኔን ከተጠጋበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ምንም በደል አላገኘሁበትም” አላቸው።