La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 4:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእግዚአብሔር ታቦት ስለ ተማረከ፣ ዐማቷና ባሏም ስለ ሞቱ፣ “ክብር ከእስራኤል ተለይቷል” ስትል የሕፃኑን ስም ኢካቦድ አለችው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የእግዚአብሔር ታቦት ስለ ተማረከ፥ ዐማቷና ባሏም ስለ ሞቱ፥ “ክብር ከእስራኤል ተለይቷአል” ስትል የሕፃኑን ስም ኢካቦድ አለችው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እርስዋም በእግዚአብሔር ታቦት መማረክ፥ በዐማትዋና በባልዋ መሞት ምክንያት ክብር ከእስራኤል ተለየ ስትል ልጅዋን ኢካቦድ ብላ ሰየመችው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ስ​ዋም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ስለ ተማ​ረ​ከች፥ ስለ አማ​ቷና ስለ ባል​ዋም፦ የሕ​ፃ​ኑን ስም ዊቦ​ር​ኮ​ኢ​ቦት ብላ ጠራ​ችው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርስዋም የእግዚአብሔር ታቦት ስለ ተማረከች ስለ አማትዋና ስለ ባልዋም፦ ክብር ከእስራኤል ለቀቀ ስትል የሕፃኑን ስም፦ ኢካቦድ ብላ ጠራችው።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 4:21
12 Referencias Cruzadas  

ክብራቸው የሆነውንም ሣር በሚበላ፣ በበሬ ምስል ለወጡ።


እግዚአብሔር ሆይ፤ የምትኖርበትን ቤት፣ የክብርህን ማደሪያ ቦታ ወደድሁ።


የኀይሉን ምልክት አስማረካት፤ ክብሩንም ለጠላቶቹ እጅ አሳልፎ ሰጠ።


ካህናታቸው በሰይፍ ተገደሉ፤ መበለቶቻቸውም ማልቀስ ተሳናቸው።


የእውነት አማልክት ባይሆኑም እንኳ፣ አማልክቱን የለወጠ ሕዝብ አለን? ሕዝቤ ግን ክብራቸው የሆነውን፣ በከንቱ ነገር ለወጡ።


ጌታ የጽዮንን ሴት ልጅ፣ በቍጣው ደመና እንዴት ጋረዳት! ከሰማይ ወደ ምድር፣ የእስራኤልን ክብር ወርውሮ ጣለው፤ በቍጣው ቀን፣ የእግሩን መቀመጫ አላስታወሰም።


ልጆችን ቢያሳድጉ እንኳ፣ ልጅ አልባ እስኪሆኑ ድረስ እነጥቃቸዋለሁ፤ ፊቴን ከእነርሱ በመለስሁ ጊዜ፣ ወዮ ለእነርሱ!


ኤፉድ ይለብስ የነበረውም አኪያ በመካከላቸው ነበር። እርሱም በሴሎ የእግዚአብሔር ካህን የነበረው የዔሊ ልጅ፣ የፊንሐስ ልጅ የኢካቦድ ወንድም የአኪጦብ ልጅ ነበር። ዮናታን አለመኖሩን ግን ያወቀ ሰው አልነበረም።


“ ‘በሁለቱ ልጆችህ በአፍኒንና በፊንሐስ ላይ የሚደርሰው ላንተ ምልክት ይሆንሃል፣ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ።


በዚያም ቀን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በዔሊና በቤተ ሰቡ ላይ የተናገርሁትን ሁሉ እፈጽማለሁ።


የእግዚአብሔር ታቦት ተማረከ፤ ሁለቱም የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ ተገደሉ።


ከዚያም፣ “የእግዚአብሔር ታቦት ተማርኳልና ክብር ከእስራኤል ተለይቷል” አለች።