1 ሳሙኤል 30:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም እንዲህ አለ፤ “ወንድሞቼ ሆይ፤ የጠበቀን፣ የመጣብንንም ወራሪ በእጃችን የጣለልን እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ በሰጠን ነገር ይህን ማድረግ አይገባችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም እንዲህ አለ፦ “ወንድሞቼ ሆይ፤ የጠበቀን፥ የመጣብንንም ወራሪ በእጃችን የጣለልን ጌታ ነው፤ እርሱ በሰጠን ነገር አስተውሉ፤ ይህን ማድረግ አይገባችሁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም “ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔር በሰጠን ድል እናንተ ይህን ማድረግ አትችሉም! እኛን በሕይወት ጠብቆ በወራሪዎች ላይ ድልን የሰጠን እርሱ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም አለ፥ “እግዚአብሔር አሳልፎ ከሰጠን በኋላ እንዲህ አታድርጉ፤ እርሱ ጠብቆናል፤ በእኛም ላይ የመጡትን ሠራዊት በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም፦ ወንድሞቼ ሆይ፥ የጠበቀን በእኛም ላይ የመጣውን ጭፍራ በእጃችን አሳልፎ የሰጠን እግዚእብሔር በሰጠን ነገር እንዲህ አታድርጉ፥ |
እስጢፋኖስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ወንድሞችና አባቶች ሆይ፤ አድምጡኝ! አባታችን አብርሃም ወደ ካራን ከመምጣቱ በፊት፣ ገና በመስጴጦምያ ሳለ፣ የክብር አምላክ ተገልጦለት፣
ነገር ግን ሀብት እንድታፈራ ችሎታ የሰጠህ፣ ለአባቶችህም በመሐላ የገባውን ኪዳን ያጸናልህ እርሱ ስለ ሆነ፣ አምላክህን እግዚአብሔርን ዐስበው።
የቤቱም ባለቤት ወደ ውጭ ወጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “የለም ወዳጆቼ፤ እንዲህ አትሁኑ፤ ሰውየው እንግዳዬ ስለ ሆነ ይህን አሳፋሪ ድርጊት አትፈጽሙ።
ከዳዊት ተከታዮች ክፉዎቹና ምናምንቴዎቹ ሁሉ ግን፣ “ዐብረውን ስላልዘመቱ ካመጣነው ምርኮ አናካፍላቸውም፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ሚስቱንና ልጆቹን ይዞ መሄድ ይችላል” አሉ።
ዳዊትም፣ “ይህን ወራሪ ሰራዊት ልከተለውን? እደርስባቸዋለሁን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፣ “በርግጥ ትደርስባቸዋለህ፤ ምርኮውንም ትመልሳለህ፤ ተከተል” ሲል መለሰለት።