Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 8:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ምናልባትም፣ “ይህን ሀብት ያፈራሁት በጕልበቴና በእጄ ብርታት ነው” ብለህ በልብህ ታስብ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በልብህም፦ ‘ጉልበቴ የእጄም ብርታት ይህን ሀብት አመጣልኝ’ እንዳትል፥ አስብ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ስለዚህም ‘ባለጸጋ የሆንኩት በራሴ ኀይልና ብርታት ነው’ ብለህ ከቶ አታስብ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በል​ብ​ህም፦ በጕ​ል​በቴ፥ በእ​ጄም ብር​ታት ይህን ሁሉ ታላቅ ኀይል አደ​ረ​ግሁ እን​ዳ​ትል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በልብህም፦ ጉልበቴ የእጄም ብርታት ይህን ሀብት አመጣልኝ እንዳትል።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 8:17
17 Referencias Cruzadas  

እጄ ባገኘችው ሀብት፣ በባለጠግነቴም ብዛት ደስ ብሎኝ ከሆነ፣


ምድሪቱን የወረሱት በሰይፋቸው አልነበረም፤ ድልንም የተጐናጸፉት በክንዳቸው አይደለም፤ አንተ ወድደሃቸዋልና ቀኝ እጅህ፣ ክንድህና የፊትህ ብርሃን ይህን አደረገ።


ለመፈለግ ጊዜ አለው፤ ለመተው ጊዜ አለው፤ ለማስቀመጥ ጊዜ አለው፤ አውጥቶ ለመጣልም ጊዜ አለው፤


ሌላም ነገር ከፀሓይ በታች አየሁ፤ ሩጫ ለፈጣኖች፣ ውጊያም ለኀያላን አይደለም፤ እንጀራ ለጥበበኞች፣ ወይም ባለጠግነት ለብልኆች፣ ወይም ሞገስ ለዐዋቂዎች አይሆንም፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል።


እንዲህ በሉ፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘የሰዎች ሬሳ፣ በሜዳ እንደ ተጣለ ጕድፍ፣ ማንም እንደማይሰበስበው፣ ከዐጫጅ ኋላ እንደ ተተወ ቃርሚያ ይወድቃል።’ ”


በንግድ ሥራ እጅግ ከመራቀቅህ የተነሣ፣ በሀብት ላይ ሀብት አካበትህ፤ ከሀብትህ ብዛት የተነሣም፤ ልብህ በትዕቢት ተወጠረ።


ስለዚህ ንጉሥ ሆይ፤ ምክሬን ስማ፤ ኀጢአት መሥራትን ትተህ ትክክለኛ የሆነውን አድርግ፤ ክፋትን ትተህ ለተጨቈኑት ቸርነትን አድርግ፤ ምናልባት በሰላም የምትኖርበት ዘመን ይራዘምልህ ይሆናል።”


“በብርቱ ኀይሌ፣ ለገናናው ክብሬ ንጉሣዊ መኖሪያ ትሆን ዘንድ ያሠራኋት ታላቂቷ ባቢሎን ይህች አይደለችምን?” አለ።


ኤፍሬም እንዲህ እያለ ይታበያል፤ “እኔ ባለጠጋ ነኝ፤ ሀብታምም ሆኛለሁ፤ ይህ ሁሉ ሀብት እያለኝ፣ ምንም ዐይነት በደል ወይም ኀጢአት አያገኙብኝም።”


ስለዚህ ለመረቡ ይሠዋል፤ ለወጥመዱም ያጥናል። በእነርሱ ተዝናንቶ ይኖራልና፤ ምግቡም ሠብቷል።


ለመሆኑ፣ አንተን ከሌላው እንድትበልጥ ያደረገህ ማን ነው? ያልተቀበልኸው የራስህ የሆነ ነገር ምን አለ? ከተቀበልህ ታዲያ፣ እንዳልተቀበልህ ለምን ትመካለህ?


“እነዚህ አሕዛብ ከእኛ ይልቅ ጠንካሮች ስለ ሆኑ፣ እንዴት አድርገን እናስወጣቸዋለን?” ብለህ በልብህ ታስብ ይሆናል።


አምላክህ እግዚአብሔር እነርሱን ከፊትህ ካስወጣቸው በኋላ በልብህ፣ “ይህችን ምድር እንድወርስ እግዚአብሔር ወደዚህ ያመጣኝ፣ ከጽድቄ የተነሣ ነው” አትበል። በዚህ አይደለም፤ እነዚህን አሕዛብ እግዚአብሔር ከፊትህ የሚያሳድዳቸው በክፋታቸው ምክንያት ነው።


እግዚአብሔር ጌዴዎንን እንዲህ አለው፤ “ምድያማውያንን በእጃቸው አሳልፌ እንዳልሰጥ ዐብረውህ ያሉት ሰዎች በጣም ብዙ ናቸው፤ እስራኤላውያን የገዛ ኀይላቸው እንዳዳናቸው በመቍጠር እንዳይታበዩብኝ፣


እግዚአብሔር ያደኸያል፤ ያበለጽጋልም፤ ያዋርዳል፤ ከፍ ከፍም ያደርጋል።


ዳዊትም እንዲህ አለ፤ “ወንድሞቼ ሆይ፤ የጠበቀን፣ የመጣብንንም ወራሪ በእጃችን የጣለልን እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ በሰጠን ነገር ይህን ማድረግ አይገባችሁም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos