1 ሳሙኤል 27:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንኩስም፣ “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” ሲል በጠየቀው ጊዜ ዳዊት፣ “የዘመትነው በይሁዳ ደቡብ፣ ወይም በይረሕምኤላውያን ደቡብ፣ ወይም በቄናውያን ደቡብ ላይ ነው” በማለት ይመልስ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አኪሽም፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” ሲል በጠየቀው ጊዜ ዳዊት፥ “የዘመትነው በይሁዳ፥ ወይም በይራሕመኤላውያን፥ ወይም በቄናውያን ላይ ነው” እያለ ይመልስለት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አኪሽ “በዚህ ጊዜ ወረራ ያደረጋችኹት በየት በኩል ነው” ብሎ ሲጠይቀው ዳዊት “እኛ የዘመትነው ከይሁዳ በስተ ደቡብ ባለው ክፍል፥ እንደገናም በይራሕመኤል ነገድ ግዛትና ቄናውያን በሚኖሩበት ግዛት ነው” እያለ ይመልስለት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንኩስም ዳዊትን፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” አለው፤ ዳዊትም፥ “በይሁዳ ደቡብ፥ በያሴሜጋ ደቡብ፥ በቄኔዛውያን ደቡብ ላይ ዘመትን” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንኩስም፦ ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ? አለ፥ ዳዊትም፦ በይሁዳ ደቡብ፥ በይረሕምኤላውያንም ደቡብ፥ በቄናውያንም ደቡብ ላይ ዘመትን አለ። |
የአቤሴሎም ሰዎች እዚያ ቤት ወደ ሴቲቱ ዘንድ መጥተው፣ “አኪማአስና ዮናታን የት አሉ?” ብለው ጠየቁ። ሴቲቱም፣ “ወንዙን ተሻግረው ሄደዋል” ብላ መለሰችላቸው፤ እነርሱም ፈልገው ስላጧቸው፣ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
የቄናዊው የሙሴ ዐማት ዝርያዎች ከዓራድ አጠገብ በኔጌብ ውስጥ በይሁዳ ምድረ በዳ ካሉት ሕዝቦች ጋራ ዐብረው ለመኖር፣ ከይሁዳ ሰዎች ጋራ በመሆን ከባለ ዘንባባዋ ከተማ ከኢያሪኮ ወጡ።
በዚያ ጊዜ ቄናዊው ሔቤር፣ የሙሴ ዐማች የኦባብ ልጆች ከሆኑት ከሌሎቹ ቄናውያን ተለይቶ በቃዴስ አጠገብ ጻዕናይም ከተባለ ቦታ ከሚገኘው ትልቅ ወርካ ጥግ ድንኳኑን ተክሎ ነበር።
እርሱም፣ ቄናውያንን፣ “ከእነርሱ ጋራ እንዳላጠፋችሁ ከአማሌቃውያን ራቁ፤ ተለዩአቸውም፤ እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ፣ ቸርነት አድርጋችሁላቸዋልና” አላቸው። ስለዚህ ቄናውያን ከአማሌቃውያን ተለዩ።
ዳዊት፣ ካህኑን አቢሜሌክን እንዲህ አለው፤ “ንጉሡ፣ ‘ስለ ላክሁህ ነገርና ስለ ሰጠሁህ መመሪያ ማንም ሰው ምንም ነገር አይወቅ’ ብሎ አዞኛል። ሰዎቼንም የት እንደምንገናኝ ነግሬያቸዋለሁ።
ዳዊት “ ‘እርሱ እንዲህ አድርጓል’ ብለው ይነግሩብናል” ብሎ ስላሰበ፣ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አስቀርቶ ወደ ጋት አላመጣም። በፍልስጥኤም ግዛት በኖረበት ዘመን ሁሉ፣ እንዲህ ማድረጉ የተለመደ ነበር።
ዳዊትም አንኩስን፣ “ለመሆኑ ምን አደረግሁ? እዚህ ከመጣሁበት ዕለት ጀምሮ እስካሁን ድረስ፣ በአገልጋይህ ላይ ምን አገኘህበት? ታዲያ፣ ከንጉሡ ከጌታዬ ጠላቶች ጋራ የማልዋጋው ስለ ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀው።