1 ሳሙኤል 22:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት ከዚያ ተነሥቶ፣ በሞዓብ ምድር ወዳለችው ወደ ምጽጳ ሄደ፤ ለሞዓብ ንጉሥ፣ “እግዚአብሔር የሚያደርግልኝን እስካውቅ ድረስ፣ አባቴና እናቴ መጥተው ካንተ ዘንድ እንዲቀመጡ ፈቃድህ ነውን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት ከዚያ ተነሥቶ፥ በሞዓብ ምድር ወዳለችው ወደ ምጽጳ ሄደ፤ ለሞዓብ ንጉሥ፥ “እግዚአብሔር የሚያደርግልኝን እስካውቅ ድረስ፥ አባቴና እናቴ መጥተው ካንተ ዘንድ እንዲቀመጡ ፈቃድህ ነውን?” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም ከዚያ ተነሥቶ በሞአብ ወደምትገኘው ወደ ምጽጳ ሄደ፤ የሞአብንም ንጉሥ “እግዚአብሔር ለእኔ የሚያደርግልኝን ነገር እስካውቅ ድረስ እባክህ አባቴና እናቴ መጥተው በአንተ ዘንድ እንዲቈዩ ፍቀድላቸው” ሲል ጠየቀው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ከዚያ በሞዓብ ምድር ወዳለችው ወደ መሴፋ ሄደ፤ የሞዓብንም ንጉሥ፥ “እግዚአብሔር የሚያደርግልኝን እስካውቅ ድረስ አባቴና እናቴ ከአንተ ጋር ይቀመጡ ዘንድ እለምንሃለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ከዚያ በሞዓብ ምድር ወዳለችው ወደ ምጽጳ ሄደ፥ የሞዓብንም ንጉሥ፦ እግዚአብሔር የሚያደርግልኝን እስካውቅ ድረስ አባቴና እናቴ ከአንተ ጋር ይቀመጡ ዘንድ እለምንሃለሁ አለው። |
እንዲሁም ዳዊት ሞዓባውያንን ድል አደረጋቸው፤ በመሬት ላይ አጋድሞ በገመድ ለካቸው፤ በገመድ ከተለኩትም ሁለት እጅ ሲገድል፣ አንድ እጅ ግን በሕይወት ይተው ነበር። ስለዚህ ሞዓባውያን የዳዊት ተገዦች ሆኑ፤ ገበሩለትም።
አንዲት መበለት ግን ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ቢኖሯት፣ እነዚህ ልጆች የራሳቸውን ቤተ ሰብ በመርዳትና ለወላጆቻቸውም ብድራትን በመመለስ ከሁሉ በፊት እምነታቸውን በተግባር ለማሳየት መማር ይገባቸዋል፤ ይህ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነውና።
ከዚያም የእግዚአብሔር መንፈስ በዮፍታሔ ላይ ወረደ፤ ተነሥቶም ገለዓድንና ምናሴን አቋርጦ ሄደ። ገለዓድ ባለችው በምጽጳ በኩል አድርጎም በአሞናውያን ላይ ዘመተባቸው።
እንዲሁም የሟቹ ስም ከወንድሞቹ መካከልና ከአገሩ ደጅ እንዳይጠፋ፣ የሟቹን ስም በርስቱ ላይ ለማስጠራት የመሐሎን ሚስት የነበረችው ሞዓባዊት ሩትን አግብቼአታለሁ፤ እናንተም ዛሬ ምስክሮች ናችሁ።”
ጎረቤቶቿ የሆኑ ሴቶችም፣ “ለኑኃሚን ወንድ ልጅ ተወለደላት” አሉ። ስሙንም ኢዮቤድ ብለው ጠሩት፤ እርሱም የዳዊት አባት የሆነው የእሴይ አባት ነበር።
ሳኦል በእስራኤል ላይ በትረ መንግሥቱን ከጨበጠ በኋላ፣ በዙሪያው ያሉትን ጠላቶቹን ማለትም ሞዓብን፣ አሞናውያንን፣ ኤዶምን፣ የሱባን ነገሥታትና ፍልስጥኤማውያንን ወጋቸው። በሄደበት ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።