1 ሳሙኤል 14:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወጣቱም ጋሻ ጃግሬ፣ “በልብህ ያሰብኸውን ሁሉ አድርግ፤ ወደ ኋላም አትበል፤ እኔም በሙሉ ልብ ካንተው ጋራ ነኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወጣቱ ጋሻ ጃግሬም፥ “በልብህ ያሰብኸውን ሁሉ አድርግ፤ ወደ ኋላም አትበል፤ እኔም በሙሉ ልብ ካንተው ጋር ነኝ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወጣቱም ጋሻጃግሬ “የምትፈቅደውን ነገር ሁሉ አድርግ፤ እኔ ከአንተ አልለይም፤ በሙሉ ልቤም ከአንተ ጋር ነኝ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጋሻ ጃግሬውም፥ “ልብህ ያሰኘህን ሁሉ አድርግ እነሆ፥ ከአንተ ጋር ነኝ፤ እንደ አንተ ልብ የእኔም ልብ እንዲሁ ነው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጋሻ ጃግሬውም፦ ልብህ ያሰኘህን ሁሉ አድርግ፥ እነሆ፥ ከአንተ ጋር ነኝ፥ እንደ አንተ ልብ ሁሉ የእኔም ልብ እንዲሁ ነው አለው። |
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በእነዚያም ቀናት ከየወገኑና ከየቋንቋው ዐሥር ሰዎች የአንድን አይሁዳዊ ልብስ ዘርፍ አጥብቀው በመያዝ፣ ‘እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ እንዳለ ሰምተናልና ዐብረን እንሂድ’ ” ይሉታል።
ወዲያውም ጋሻ ጃግሬውን ጠርቶ፣ “ ‘ሴት ገደለችው’ እንዳይሉ እባክህ ሰይፍህን መዝዘህ ግደለኝ” አለው። ስለዚህ አገልጋዩ ወጋው፤ እርሱም ሞተ።
ዮናታን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፣ “ና፤ ወደነዚያ ሸለፈታሞች ጦር ሰፈር እንሻገር፤ ምናልባትም እግዚአብሔር ይዋጋልን ይሆናል፤ በብዙም ሆነ በጥቂት ለማዳን እግዚአብሔርን የሚያግደው የለምና” አለው።