1 ሳሙኤል 14:47 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል በእስራኤል ላይ በትረ መንግሥቱን ከጨበጠ በኋላ፣ በዙሪያው ያሉትን ጠላቶቹን ማለትም ሞዓብን፣ አሞናውያንን፣ ኤዶምን፣ የሱባን ነገሥታትና ፍልስጥኤማውያንን ወጋቸው። በሄደበት ሁሉ ድል ይነሣ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል በእስራኤል ላይ ከነገሠ በኋላ፥ በዙሪያው ያሉትን ጠላቶቹን ሞዓብን፥ አሞናውያንን፥ ኤዶምን፥ የጾባን ነገሥታትና ፍልስጥኤማውያንን ወጋቸው። በተዋጋበት ስፍራ ሁሉ ድል አድራጊ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል በእስራኤል ከነገሠ በኋላ፥ በሁሉም ስፍራ የሚገኙ ጠላቶቹን ወጋ፤ እነርሱም የሞአብ፥ የዐሞንና የኤዶም ሕዝቦች፥ የጾባ ነገሥታትና ፍልስጥኤማውያን ናቸው፤ በተዋጋበት ስፍራ ሁሉ ድል አድራጊ ሆነ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም መንግሥቱን በእስራኤል ላይ አጸና፤ በዙሪያውም ካሉት ከጠላቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞዓብም፥ ከአሞንም ልጆች፥ ከኤዶምያስም፥ ከቢዖርም፥ ከሱባም ነገሥታት፥ ከፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር፤ በየሄደበትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም መንግሥቱን በእስራኤል ላይ አጸና፥ በዙሪያውም ካሉት ከጠላቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞዓብም፥ ከአሞንም ልጆች፥ ከኤዶምያስም፥ ከሱባም ነገሥታት፥ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ይዋጋ ነበር፥ በየሄደበትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር። |
አሞናውያን፣ ዳዊት እንደ ጠላቸው ባወቁ ጊዜ፣ ከቤትሮዖብና ከሱባ ሃያ ሺሕ ሶርያውያን እግረኛ ወታደሮችን እንዲሁም የመዓካን ንጉሥ ከአንድ ሺሕ ሰዎቹ ጋራ ደግሞም ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺሕ ሰዎች ቀጠሩ።
ንጉሥ ሆኖ የሚመራችሁንም ሰው እነሆ፤ አግኝታችኋል። እኔም ዕድሜዬ ገፍቷል፤ ጠጕሬም ሸብቷል፤ ልጆቼም ዐብረዋችሁ አሉ፤ ከወጣትነት ጊዜዬ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ስመራችሁ ቈይቻለሁ።
በሳኦል ዘመን ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋራ ከባድ ጦርነት ነበረ፤ ስለዚህ ሳኦል ብርቱ ወይም ጀግና ሰው ባየ ቍጥር ወደ ራሱ ወስዶ እንዲያገለግለው ያደርግ ነበር።