1 ሳሙኤል 13:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ፤ እስራኤልንም አርባ ሁለት ዓመት ገዛ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል በእስራኤልም ላይ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፥ እንዲህ ሆነ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል ሲነግሥ ዕድሜው 30 ዓመት ነበር፤ በእስራኤልም ላይ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም በእስራኤል ላይ ከነገሠ ሁለት ዓመት ሆነው፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም በእስራኤል ላይ ሁለት ዓመት ከነገሠ በኋላ፥ |
ሳኦል ከእስራኤል ሦስት ሺሕ ሰዎች መረጠ። ሁለቱ ሺሕ በማክማስና በኰረብታማው አገር በቤቴል ከሳኦል ጋራ፣ አንዱ ሺሕ ደግሞ በብንያም ግዛት በጊብዓ ከዮናታን ጋራ ነበሩ። የቀሩትን ሰዎች ግን ወደ የቤታቸው እንዲሄዱ አሰናበተ።