ሶፎንያስ 1:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤን አሳልፌ በምሰጥበት ቀን ልዑላኑንና ባለ ሥልጣኖችን እንዲሁም የባዕድ ባህል የሚከተሉትን ሁሉ እቀጣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በእግዚአብሔር የመሥዋዕት ቀን፣ መሳፍንቱንና የንጉሡን ልጆች፣ እንግዳ ልብስ የሚለብሱትን ሁሉ እቀጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ የመሥዋዕት ቀን ባለ ሥልጣኖችንና የንጉሡን ልጆች፥ እንግዳ ልብስ የሚለብሱትንም ሁሉ እበቀላለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔርም መሥዋዕት ቀን አለቆችንና የንጉሥን ልጆች እንግዳ ልብስ የሚለብሱትንም ሁሉ እቀጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔርም መሥዋዕት ቀን አለቆችንና የንጉሥን ልጆች እንግዳ ልብስ የሚለብሱትንም ሁሉ እቀጣለሁ። |
ነገር ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “በኢየሩሳሌምና በጽዮን ተራራ የማደርገውን ሁሉ ከፈጸምኩ በኋላ ስለ ትምክሕቱና ስለ ትዕቢቱ ሁሉ ብዛት የአሦርንም ንጉሠ ነገሥት ደግሞ እቀጣለሁ።”
አምላክ ሆይ! የያዕቆብ ዘሮች የሆኑ ሕዝብህን እርግፍ አድርገህ ትተሃል፤ ምድሪቱ በምሥራቅ አገር ሰዎች ጥንቈላና በፍልስጥኤማውያን ሟርት ተሞልታለች፤ ሕዝቡም ከአሕዛብ ጋር ተባብረዋል።