ዘካርያስ 9:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአስቀሎና ከተማ ይህን አይታ ትፈራለች፤ የጋዛ ከተማም ይህን በማየት እጅግ ትጨነቃለች፤ ዔቅሮንም እንዲሁ ተስፋ ትቈርጣለች፤ ጋዛ ንጉሥዋን ታጣለች፤ አስቀሎናም ምድረ በዳ ሆና ትቀራለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አስቀሎና አይታ ትርዳለች፤ ጋዛ በሥቃይ ትቃትታለች፤ አቃሮናም እንደዚሁ ትሠቃያለች፤ ተስፋዋ ይመነምናልና። ጋዛ ንጉሥዋን ታጣለች፤ አቃሮንም ባድማ ትሆናለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አስቀሎና አይታ ትፈራለች፤ ጋዛ በሥጋት ትታመማለች፤ እንዲሁም አቃሮን፥ ተስፋዋ ይመነምናል። ንጉሡም ከጋዛ ይጠፋል፥ በአስቀሎናም የሚኖር አይገኝም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አስቀሎና አይታ ትፈራለች፣ ጋዛ ደግሞ አይታ እጅግ ትታመማለች፣ አቃሮንም እንዲሁ፥ ተስፋዋ ይቈረጣልና፣ ንጉሡም ከጋዛ ይጠፋል፥ በአስቀሎናም የሚቀመጥ አይገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አስቀሎና አይታ ትፈራለች፥ ጋዛ ደግሞ አይታ እጅግ ትታመማለች፥ አቃሮንም እንዲሁ፥ ተስፋዋ ይቈረጣልና፥ ንጉሡም ከጋዛ ይጠፋል፥ በአስቀሎናም የሚቀመጥ አይገኝም። |
“እናንተ የጢሮስ፥ የሲዶናና የፍልስጥኤም አውራጃዎች ሕዝብ ሆይ፥ ምን እያደረጋችሁ ነው? እኔን ለመበቀል ይቃጣችኋልን? ይህ ከሆነ ሥራችሁ ወዲያው በፍጥነት በራሳችሁ ላይ እንዲመለስ አደርጋለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የጋዛ ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ እነርሱ የሀገሩን ሕዝብ ሁሉ ከማረኩ በኋላ ለኤዶም ሰዎች አሳልፈው ሰጥተዋቸዋል።
በፍጹም እንደማላፍር በተስፋ እጠባበቃለሁ፤ ነገር ግን ዘወትር እንደማደርገውና ዛሬ በሕይወት ብኖር ወይም ብሞት ክርስቶስ በሰውነቴ ይከብራል ብዬ በድፍረት እናገራለሁ።