ዘካርያስ 3:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልአኩም አገልጋዮቹን “ንጹሕ ጥምጥም በራሱ ላይ አድርጉለት!” ብሎ አዘዘ፤ እነርሱም እንደ ታዘዙት አደረጉ፤ የእግዚአብሔር መልአክ እዚያው ቆሞ እንዳለ አገልጋዮቹ ኢያሱን አዲስ ልብስ አለበሱት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም፣ “ንጹሕ ጥምጥም በራሱ ላይ አድርጉለት” አልሁ። የእግዚአብሔርም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ እያለ፣ ንጹሕ ጥምጥም በራሱ ላይ አደረጉለት፤ ልብስም አለበሱት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም፥ “ንጹሕ የራስ ላይ ጥምጣም ያድርጉለት” አለ። እነርሱም በራሱ ላይ ንጹሕ ጥምጥም አደረጉ፥ ልብስንም አለበሱት፤ የጌታም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞ፦ ንጹሕ ጥምጥም በራስ ላይ አድርጉ አለ። እነርሱም በራሱ ላይ ንጹሕ ጥምጥም አደረጉ፥ ልብስንም አለበሱት፣ የእግዚአብሔርም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ፦ ንጹሕ ጥምጥም በራስ ላይ አድርጉ አለ። እነርሱም በራሱ ላይ ንጹሕ ጥምጥም አደረጉ፥ ልብስንም አለበሱት፥ የእግዚአብሔርም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ ነበር። |
እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ ሁለንተናዬም በአምላኬ ሐሴትን ያደርጋል፤ የአበባ አክሊል በራሱ ላይ እንደሚያደርግ ሙሽራ፥ በጌጣጌጥም እንዳሸበረቀች ሙሽሪት አድርጎ፥ የመዳንን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።
ካህናቱ ወደተቀደሰው ቦታ ገብተው የሚያገለግሉባቸውን ልብሶች ከለበሱ በኋላ ያን ያገልግሎት ልብስ ሳያወልቁ ወደ ውጪው አደባባይ አይወጡም፤ ልብሶቹም የተቀደሱ ስለ ሆኑ ከተቀደሰው ቦታ ወጥተው ለሕዝብ ወደተፈቀደው ቦታ ከመድረሳቸው በፊት ሌላ ልብስ መልበስ ይኖርባቸዋል።”
ኻያ አራቱ ሽማግሌዎች ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሚኖረው፥ በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ፊት በግንባራቸው ተደፍተው ይሰግዳሉ፤ አክሊሎቻቸውንም በዙፋኑ ፊት አኑረው፥ እንዲህ ይላሉ፦
እንዲሁም፥ በዙፋኑ ዙሪያ ኻያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፤ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ የለበሱና በራሳቸው ላይ የወርቅ አክሊል የደፉ ኻያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።