ዐዛርያስም ከንጉሥ አሳ ጋር ለመገናኘት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “ንጉሥ አሳ ሆይ! አድምጠኝ! እናንተም የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ስሙኝ! እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር እስከ ሆናችሁ ድረስ እርሱም ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ከፈለጋችሁትም ታገኙታላችሁ፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል፤
ዘካርያስ 1:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁን ግን እናንተን የምላችሁ ይህ ነው፦ ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ለሕዝቡ ንገር፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ወደ እኔ ተመለሱ፤’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ‘እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፤’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ “የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል ወደ እኔ ተመለሱ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ እኔ ተመለሱ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ እኔ ተመለሱ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። |
ዐዛርያስም ከንጉሥ አሳ ጋር ለመገናኘት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “ንጉሥ አሳ ሆይ! አድምጠኝ! እናንተም የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ስሙኝ! እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር እስከ ሆናችሁ ድረስ እርሱም ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ከፈለጋችሁትም ታገኙታላችሁ፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል፤
ነገር ግን ሰላም ባገኙ ጊዜ እንደገና ኃጢአት ሠሩ፤ አንተም እንደገና ድል ለሚነሡ ጠላቶቻቸው ተውካቸው እነርሱም ገዙአቸው፤ ነገር ግን አንተ እንድትረዳቸው እንደገና በጠየቁ ጊዜ በሰማይ ሆነህ ሰማሃቸው፤ ከርኅራኄህም የተነሣ በየጊዜው ታደግኻቸው።
ነገር ግን ከአገራቸው ካወጣኋቸው በኋላ እንደገና ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ እያንዳንዱንም ሕዝብ ወደ ገዛ ምድሩና ወደ ገዛ አገሩ መልሼ አመጣዋለሁ።
እነርሱም ‘እግዚአብሔር ለእናንተና ለቀድሞ አባቶቻችሁ በሰጣት በዚህች ምድር ለዘለዓለም መኖር ትችሉ ዘንድ ከመጥፎ አኗኗራችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰው ሚስቱን ቢፈታ፥ እርስዋም ከእርሱ ተለይታ ሌላ ወንድ ካገባች በኋላ እንደገና መልሶ ሊያገባት ይችላልን? ይህ ቢደረግማ ፈጽሞ ምድርን የሚያረክስ ይሆናል። እስራኤል ሆይ! አንቺ ግን ብዙ ጣዖቶችን ወደሽ ነበር፤ አሁን ደግሞ እንደገና ወደ እኔ መመለስ ትፈልጊያለሽ።
እናንተ ከእግዚአብሔር ርቃችሁ የነበራችሁ ሁሉ ተመለሱ፤ እርሱ ይፈውሳችኋል፤ ታማኞችም ያደርጋችኋል። እናንተም እንዲህ ብላችኋል፦ “አዎ! እግዚአብሔር አምላካችን ስለ ሆነ ወደ እርሱ እንመለሳለን፤
አገልጋዮቼ የሆኑትን ነቢያትን ወደ እናንተ ደጋግሜ ልኬአለሁ፤ እነርሱም ከክፉ ሥራችሁ ተመልሳችሁ ቅን የሆነውን ነገር እንድትሠሩ ነግረዋችኋል፤ ለባዕዳን አማልክት እንዳትሰግዱና የእነርሱም አገልጋዮች እንዳትሆኑ አስጠንቅቀዋችኋል፤ ለእናንተና ለቀድሞ አባቶቻችሁ በሰጠኋችሁ ምድር መኖር ትችሉ ዘንድ ይህን ሁሉ አዘዝኳችሁ፤ እናንተ ግን እኔን ለማዳመጥም ሆነ ለምነግራችሁ ቃል ትኲረት ልትሰጡት አልፈለጋችሁም።
እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ወደ እኔ ለመመለስ ከፈለጋችሁ እነዚያን አጸያፊ ጣዖቶችን አስወግዳችሁ ለእኔ ብቻ ታማኞች ብትሆኑ፥
“ ‘ታዲያ ልጁ በአባቱ ኃጢአት ምክንያት ያልተቀጣው ስለምንድን ነው?’ ትሉ ይሆናል፤ ልጁ ትክክልና መልካም የሆነውን ነገር አድርጎአል፤ ሕጌን አክብሮአል፤ ስለዚህ እርሱ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል፤
እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ ኃጢአተኛ ሰው፥ ኃጢአት መሥራቱን ትቶ በሕይወት እንዲኖር እንጂ በኃጢአቱ እንዲሞት አልፈቅድም፤ ስለዚህ እስራኤል ሆይ! ክፉ ሥራችሁን ተዉ፤ መሞትን ለምን ትፈልጋላችሁ? ብለህ ንገራቸው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የሕዝቤን አለመታመን ፈውሼ፤ ወደ እኔ እመልሳቸዋለሁ ቊጣዬ ከእነርሱ ስለ ተመለሰ፥ እኔ በገዛ ፈቃዴ እወዳቸዋለሁ፤
ከቀድሞ አባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከሕጌ ርቃችኋል፤ አልጠበቃችሁትምም። ‘ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ’፥ እናንተ ግን ‘ወደ አንተ የምንመለሰው በምን ዐይነት ነው?’ ትላላችሁ።