Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ነህምያ 9:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ነገር ግን ሰላም ባገኙ ጊዜ እንደገና ኃጢአት ሠሩ፤ አንተም እንደገና ድል ለሚነሡ ጠላቶቻቸው ተውካቸው እነርሱም ገዙአቸው፤ ነገር ግን አንተ እንድትረዳቸው እንደገና በጠየቁ ጊዜ በሰማይ ሆነህ ሰማሃቸው፤ ከርኅራኄህም የተነሣ በየጊዜው ታደግኻቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 “ነገር ግን ዕረፍት ባገኙ ጊዜ፣ በፊትህ ክፉውን ነገር እንደ ገና ፈጸሙ፤ ከዚያም ይገዟቸው ዘንድ በጠላቶቻቸው እጅ ጣልሃቸው፤ እንደ ገና ወደ አንተ በጮኹ ጊዜ፣ ከሰማይ ሰማህ፤ በርኅራኄህም በየጊዜው ታደግሃቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ባረፉም ጊዜ ተመልሰው በፊትህ ክፉ አደረጉ፥ በጠላቶቻቸው እጅ ተውካቸው፥ ገዙአቸውም፥ ተመልሰውም ወደ አንተ በጮኹ ጊዜ ከሰማይ ሰማሃቸው፥ እንደ ምሕረትህም ብዛት ታደግሃቸው፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ባረ​ፉም ጊዜ ተመ​ል​ሰው በፊ​ትህ ክፉ አደ​ረጉ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅ ተው​ሃ​ቸው፤ ገዙ​አ​ቸ​ውም፤ ተመ​ል​ሰ​ውም ወደ አንተ በጮኹ ጊዜ ከሰ​ማይ ሰማ​ሃ​ቸው፤ እንደ ምሕ​ረ​ት​ህም ብዛት ታደ​ግ​ሃ​ቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ባረፉም ጊዜ ተመልሰው በፊትህ ክፉ አደረጉ፥ በጠላቶቻቸው እጅ ተውሃቸው፥ ገዙአቸውም፥ ተመልሰውም ወደ አንተ በጮኹ ጊዜ ከሰማይ ሰማሃቸው፥ እንደ ምሕረትህም ብዛት ታደግሃቸው፥

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 9:28
12 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሆይ! ጠላቶችህን ሁሉ በዚህ ዐይነት አጥፋ፤ ወዳጆችህ ግን እንደ ንጋት ፀሐይ ይድመቁ። ከዚህ በኋላ በምድሪቱ ላይ አርባ ዓመት ሙሉ ሰላም ሆነ።


ጸሎታቸውን ስማ፤ በምትኖርበት በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን በመስማት በደላቸውን ይቅር በላቸው፤ ርዳቸውም፤ በሰው ልብና አእምሮ ያለውን ሐሳብ ሁሉ መርምረህ የምታውቅ አንተ ብቻ ነህ፤ ስለዚህ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን የሚገባውን ዋጋ ስጠው፤


ኤሁድ ከሞተ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ እንደገና በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠሩ፤


በዚያን ቀን ሞአባውያን በእስራኤላውያን ድል ተመቱ፤ በምድሪቱም ላይ ሰማኒያ ዓመት ሙሉ ሰላም ሆነ።


እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! ከተቀደሰውና ከክቡር መኖሪያህ ከሰማይ ወደ ታች ተመልከት፤ ቅንአትህና ኀይልህ የት አሉ? መልካም ፈቃድህና ርኅራኄህስ የት አለ? እነርሱ ከእኛ ርቀዋል።


ከጠላቶቻችን እጅ ነጻ አወጣን፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።


ነገር ግን መሪ በሚሞትበት ጊዜ ሁሉ ተመልሰው ሌሎች አማልክትን በመከተል፥ ለእነርሱም በመስገድና እነርሱንም በማምለክ ከአባቶቻቸው የከፋ በደል ይፈጽሙ ነበር፤ መጥፎ ድርጊታቸውንና ልበ ደንዳና መሆናቸውን አልተዉም።


በጠላቶቻቸው ተጨቊነው ፈጽሞ የእነርሱ ተገዢዎች ሆኑ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios