ዘካርያስ 1:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ለከተማይቱ ምሕረትን ለማሳየት ወደ ኢየሩሳሌም እመለሳለሁ ቤተ መቅደሴና ከተማይቱ እንደገና ታድሰው ይሠራሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በምሕረት ወደ ኢየሩሳሌም እመለሳለሁ፤ በዚያም ቤቴ እንደ ገና ይሠራል፤ መለኪያ ገመድም በኢየሩሳሌም ላይ ይዘረጋል’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ወደ ኢየሩሳሌም በምሕረት ተመልሻለሁ፤ ቤቴ መልሶ ይገነባባታል፤ በኢየሩሳሌምም ላይ መለኪያ ገመድ ይዘረጋበታል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ኢየሩሳሌም በምሕረት ተመልሻለሁ፣ ቤቴ ይሠራባታል፣ በኢየሩሳሌምም ላይ ገመድ ይዘረጋበታል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ኢየሩሳሌም በምሕረት ተመልሻለሁ፥ ቤቴ ይሠራባታል፥ በኢየሩሳሌምም ላይ ገመድ ይዘረጋበታል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። |
ጭልፊትና ጃርት ይወርሱአታል፤ የጒጒትና የቊራም መጮኺያ ትሆናለች፤ በላይዋም የመፍረስዋ መለኪያ የሆነ ገመድና የባዶነትዋ መመዘኛ የሆነ ቱምቢ ይዘረጉባታል፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልን ልጆች ቤት መልሼ እሠራለሁ፤ ለያንዳንዱም ቤተሰብ ምሕረቴን እልካለሁ፤ የኢየሩሳሌም ከተማ እንደገና ትሠራለች፤ ቤተ መንግሥቱም በድሮ ቦታ ተመልሶ ይታነጻል።
ወደዚያ ሲወስደኝም እንደ ነሐስ የሚያበራ መልክ ያለውን አንድ ሰው አየሁ፤ እርሱም ከበፍታ የተሠራ ገመድና መለኪያ ዘንግ ይዞ በቅጽሩ በር አጠገብ ቆሞ ነበር።
ያም ሰው በያዘው የመለኪያ ገመድ ወደ ምሥራቅ የሚፈሰውን ውሃ በመከተል አንድ ሺህ ክንድ ለካ፤ በዚያም ውሃ እየተራመድኩ እንድሻገር አደረገኝ፤ ውሃውም እስከ ቊርጭምጭሚቴ ደረሰ።
በአራቱም አቅጣጫ ያሉት የከተማይቱ የቅጽር ግንቦች ጠቅላላ ርዝመት ዐሥራ ስምንት ሺህ ክንድ ይሆናል፤ ከአሁን በኋላ የከተማይቱ መጠሪያ ስም “እግዚአብሔር በዚያ አለ!” የሚል ይሆናል።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር የይሁዳ ገዢ የሆነውን የሰላትያልን ልጅ ዘሩባቤልን፥ ሊቀ ካህናቱን የኢዮሴዴቅን ልጅ ኢያሱንና ተርፈው ከስደት የተመለሱትን ሰዎች ሁሉ መንፈስ አነሣሣ፤ እነርሱም የአምላካቸውን የሠራዊትን ጌታ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሥራት ጀመሩ።
“እኔ የይሁዳን ሕዝብ ብርቱ አደርጋለሁ፤ የእስራኤልንም ሕዝብ እታደጋለሁ፤ ስለምራራላቸውም ሁሉንም ወደ አገራቸው እመልሳለሁ፤ ከዚህ በፊት ከቶ ጥዬአቸው እንደማላውቅ ይሆናሉ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ስለ ሆንኩ ጸሎታቸውን እሰማለሁ።
የመጀመሪያው መልአክ ሁለተኛውን እንዲህ አለው፦ “የመለኪያ ገመድ ወደያዘው ወጣት በሩጫ ሂድና ‘በኢየሩሳሌም ብዙ ሕዝብና ብዙ እንስሶች ስለሚገኙ ትልቅ ግንብ መሥራት ያዳግታል’ ብለህ ንገረው።
“የዘሩባቤል እጆች የዚህን ቤተ መቅደስ መሠረት ጥለዋል፤ እጆቹም ይፈጽሙታል፤ ያን ጊዜ የሠራዊት አምላክ እኔን ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።
እኔ እንድኖርባት ወደ ተቀደሰችው ከተማዬ ወደ ኢየሩሳሌም እመለሳለሁ፤ የታመነች ከተማ በመሆን ትታወቃለች፤ እኔ የሠራዊት አምላክ የምኖርበት ተራራ፥ የተቀደሰ ተራራ ተብሎ ይጠራል፤