ሩት 4:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውየውም “ይህን ብወስድ የራሴን ድርሻ የሚጐዳ ስለ ሆነ እኔ ልወስደው አልፈልግምና አንተ እንድትወስደው ፈቅጄልሃለሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያም ቅርብ የሥጋ ዘመድ፣ “እንዲህ ከሆነማ የራሴን ርስት አደጋ ላይ ልጥል ስለምችል፣ እኔ ልቤዠው አልችልም፤ አንተው ራስህ ተቤዠው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቅርብ ዘመዱም፦ “የራሴን ርስት እንዳላበላሽ መውሰድ አልችልም፥ እኔ የራሴ ላደርገው አልችልምና አንተ እንድትወስደው ፈቅጄልሃለሁ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቅርብ ዘመዱም፦ የራሴን ርስት እንዳላበላሽ መቤዠት አልችልም፣ እኔ መቤዠቱን አልችልምና አንተ ከእኔ መቤዠቱን ውሰደው አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቅርብ ዘመዱም “የራሴን ርስት እንዳላበላሽ መቤዠት አልችልም፤ እኔ መቤዠቱን አልችልምና አንተ ከእኔ መቤዠቱን ውሰደው፤” አለ። |
ነገር ግን የሟቹ ወንድም እርስዋን ለማግባት ባይፈልግ፥ ወደ ከተማይቱ መሪዎች ዘንድ ሄዳ ‘የባሌ ወንድም ግዴታውን ለመፈጸም ፈቃደኛ አልሆነም፤ ለሟቹ ወንድም በእስራኤል ሕዝብ መካከል ዘር ለመተካት ፈቃደኛ አልሆነም’ በማለት ታስረዳ፤
የሟቹ ሚስት በከተማይቱ መሪዎች ፊት ወደ እርሱ ትቅረብ፤ ከእግሩ ጫማዎች አንዱን አውልቃ ምራቋን በፊቱ ላይ በመትፋት ‘ለወንድሙ ዘር ለመተካት እምቢ ለሚል ሰው ይህን ዐይነት አሳፋሪ ነገር ሊፈጸምበት ይገባል’ ትበል።
ናዖሚም “ለሕያዋንና ለሙታን የሰጠውን ተስፋ የሚፈጽም አምላክ ቦዔዝን ይባርከው!” አለች፤ ቀጥላም “ያ ሰው እኮ የቅርብ ዘመዳችን ነው! እንዲያውም ለእኛ ኑሮ የማሰብ ኀላፊነት ካለባቸው ሰዎች አንዱ እርሱ ነው” አለች።
እስኪነጋ እዚሁ ቈዪ! ሲነጋም ያ ሰው ስለ አንቺ ኀላፊነትን የሚወስድ መሆኑን ወይም አለመሆኑን እጠይቀዋለሁ፤ እርሱ ኀላፊነትን የሚወስድ ከሆነ መልካም ነው፤ የማይወስድ ከሆነ ግን ስለ አንቺ ኀላፊነትን እኔ እንደምወስድ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ አሁንም ተኚ፤ እስኪነጋም ድረስ እዚሁ ቈዪ።”
“አንቺ ማን ነሽ?” ብሎም ጠየቃት። እርስዋም “ጌታዬ ሆይ! አገልጋይህ እኔ ሩት ነኝ፤ አንተ የቅርብ ዘመድ ስለ ሆንክ ለእኔ ኑሮ የማሰብ ኀላፊነት አለብህ፤ ስለዚህ ልብስህን ባገልጋይህ ላይ ጣል አለችው።”