ከዚህም በኋላ እርስዋ ደብዳቤ ጽፋ በአክዓብ ስም ፈርማ የእርሱኑ ማኅተም አተመችበት፤ ደብዳቤውንም ናቡቴ ወደሚኖርባት ወደ ኢይዝራኤል ባለሥልጣኖችና ሽማግሌዎች ላከች።
ሩት 4:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ቦዔዝ ከከተማው ሽማግሌዎች ዐሥሩን መርጦ “እዚህ ተቀመጡ” አላቸው፤ እነርሱም ተቀመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቦዔዝ ከከተማዪቱ ሽማግሌዎች ዐሥሩን ጠርቶ፣ “እዚህ ተቀመጡ” አላቸው፤ እነርሱም ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቦዔዝም ከከተማይቱ ሽማግሌዎች ዐሥር ሰዎች ጠርቶ፦ “በዚህ ተቀመጡ” አላቸው። እነርሱም ተቀመጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቦዔዝም ከከተማይቱ ሽማግሌዎች አሥር ሰዎች ጠርቶ፦ በዚህ ተቀመጡ አላቸው። እነርሱም ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቦዔዝም ከከተማይቱ ሽማግሌዎች ዐሥር ሰዎች ጠርቶ “በዚህ ተቀመጡ፤” አላቸው። |
ከዚህም በኋላ እርስዋ ደብዳቤ ጽፋ በአክዓብ ስም ፈርማ የእርሱኑ ማኅተም አተመችበት፤ ደብዳቤውንም ናቡቴ ወደሚኖርባት ወደ ኢይዝራኤል ባለሥልጣኖችና ሽማግሌዎች ላከች።
ሚስት ሊያደርጋት ለፈለገ ሰው ብትሸጥና በኋላም እርሱ ሳይወዳት ቢቀር ተመልሳ በሕዝብዋ ትዋጅ ጌታዋ የማይገባ ነገር ስላደረገባት ለባዕድ ሊሸጣት አይችልም።
ነገር ግን የሟቹ ወንድም እርስዋን ለማግባት ባይፈልግ፥ ወደ ከተማይቱ መሪዎች ዘንድ ሄዳ ‘የባሌ ወንድም ግዴታውን ለመፈጸም ፈቃደኛ አልሆነም፤ ለሟቹ ወንድም በእስራኤል ሕዝብ መካከል ዘር ለመተካት ፈቃደኛ አልሆነም’ በማለት ታስረዳ፤
“እነሆ፥ ዛሬ እናንተ የየነገድ መሪዎቻችሁ፥ ሽማግሌዎቻችሁ፥ ሹሞቻችሁ፥ ሌሎችም የእስራኤል ወንዶች ሁሉና ልጆቻችሁ፥ ሴቶቻችሁ፥ በእናንተ ሰፈር ሆነው እንጨት የሚለቅሙላችሁና ውሃ የሚቀዱላችሁ መጻተኞች፥ ሁላችሁም በእግዚአብሔር አምላካችሁ ፊት ቆማችኋል።
ስለዚህም ይህን ሁሉ እነግራቸው ዘንድ የነገድ መሪዎቻችሁንና የሕዝብ አለቆችን ሰብስቡልኝ፤ እኔ ሰማይንና ምድርን በእነርሱ ላይ ምስክሮች አድርጌ እጠራለሁ።