የሕዝቤን አካሄድ በሙሉ ልባቸው ተቀብለው እነርሱ ከዚህ በፊት ሕዝቤን በባዓል ስም መማል እንዳስተማሩአቸው ዐይነት ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው የሚምሉ ከሆነ በሕዝቤ መካከል እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ፤
ሩት 3:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስኪነጋ እዚሁ ቈዪ! ሲነጋም ያ ሰው ስለ አንቺ ኀላፊነትን የሚወስድ መሆኑን ወይም አለመሆኑን እጠይቀዋለሁ፤ እርሱ ኀላፊነትን የሚወስድ ከሆነ መልካም ነው፤ የማይወስድ ከሆነ ግን ስለ አንቺ ኀላፊነትን እኔ እንደምወስድ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ አሁንም ተኚ፤ እስኪነጋም ድረስ እዚሁ ቈዪ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ ዕደሪ፤ ሲነጋም ሰውየው ሊቤዥሽ ከፈለገ፣ መልካም ነው፤ ይቤዥሽ፤ የማይፈልግ ከሆነ ግን በሕያው እግዚአብሔር እምላለሁ፤ እኔ እቤዥሻለሁ፤ እስኪነጋም ድረስ እዚሁ ተኚ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዛሬ ሌሊት እደሪ፥ ነገም እርሱ ዋርሳ መሆን ቢወድ መልካም ነው፥ ዋርሳ ይሁን፥ ዋርሳ ሊሆን ባይወድ ግን፥ ሕያው ጌታን እኔ ዋርሳ እሆንሻለሁ፥ እስኪ ነጋ ድረስ ተኚ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛሬ ሌሊት እደሪ፣ ነገም እርሱ ዋርሳ መሆን ቢወድድ መልካም ነው፥ ዋርሳ ይሁን፣ ዋርሳ ሊሆን ባይወድድ ግን፥ ሕያው እግዚአብሔርን እኔ ዋርሳ እሆንሻለሁ፣ እስኪነጋ ድረስ ተኚ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛሬ ሌሊት እደሪ፤ ነገም እርሱ ዋርሳ መሆን ቢወድድ መልካም ነው፤ ዋርሳ ይሁን፤ ዋርሳ ሊሆን ባይወድድ ግን፥ ሕያው እግዚአብሔርን! እኔ ዋርሳ እሆንሻለሁ፤ እስኪነጋ ድረስ ተኚ።” |
የሕዝቤን አካሄድ በሙሉ ልባቸው ተቀብለው እነርሱ ከዚህ በፊት ሕዝቤን በባዓል ስም መማል እንዳስተማሩአቸው ዐይነት ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው የሚምሉ ከሆነ በሕዝቤ መካከል እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ፤
ጌዴዎንም “እነርሱ የእናቴ ልጆች ወንድሞቼ ነበሩ፤ እናንተ እነርሱን ባትገድሉ ኖሮ እኔም ምሕረት አደርግላችሁ እንደ ነበር በእርግጥ እምላለሁ” አላቸው።
ናዖሚም “ለሕያዋንና ለሙታን የሰጠውን ተስፋ የሚፈጽም አምላክ ቦዔዝን ይባርከው!” አለች፤ ቀጥላም “ያ ሰው እኮ የቅርብ ዘመዳችን ነው! እንዲያውም ለእኛ ኑሮ የማሰብ ኀላፊነት ካለባቸው ሰዎች አንዱ እርሱ ነው” አለች።
ቦዔዝም “መሬቱን ከናዖሚ የምትገዛ ከሆነ በውርሱ የሟቹን ስም ታስጠራ ዘንድ ባልዋ የሞተባትን ሞአባዊትዋን ሩትንም አብረህ ትወስዳለህ” አለው።