ሮሜ 9:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ጽድቅ የሚያስገኘውን ሕግ ይከተሉ የነበሩት እስራኤላውያን ሕግን ለመፈጸም ባለመቻላቸው ወደ ጽድቅ አልደረሱም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን የጽድቅን ሕግ የተከታተሉት እስራኤል አላገኙትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እስራኤል የጽድቅን ሕግ እየተከተለ ወደ ሕግ አልደረሰም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤል ግን ኦሪትን ሲከተሉ መጽደቅ ተሳናቸው፤ የኦሪታቸውን ሥራ አልፈጸሙምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤል ግን የጽድቅን ሕግ እየተከተሉ ወደ ሕግ አልደረሱም። |
እንግዲህ የምንመካበት ነገር ምን አለ? በምንም አንመካም! የማንመካበትስ ምክንያት ምንድን ነው? ሕግን ስለምንፈጽም ነውን? አይደለም፤ ነገር ግን በእምነት ነው።
እንግዲህ ሕግ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ይቃወማልን? ከቶ አይቃወምም! ሕይወት የሚገኝበት ሕግ ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ ጽድቅ በሕግ አማካይነት በተገኘ ነበር።