Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሮሜ 9:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 እንግዲህ ምን እንላለን? ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፤ ይህም ጽድቅ ከእምነት የሚገኘው ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 እንግዲህ ምን እንበል? በእምነት የሆነውን ጽድቅ፣ ለጽድቅ ያልደከሙት አሕዛብ አገኙት፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 እንግዲህ ምን እንላለን? አሕዛብ ጽድቅን ሳይከተሉ ጽድቅን አገኙ፤ እርሱም በእምነት የሆነ ጽድቅ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? ጽድ​ቅን ያል​ፈ​ለ​ጉ​አት አሕ​ዛብ ስንኳ ጽድ​ቅን አገ​ኙ​አት፤ በእ​ም​ነ​ትም ጸደቁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 እንግዲህ ምን እንላለን? ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፥ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው፤

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 9:30
28 Referencias Cruzadas  

ይህንንም የማደርግበት ምክንያት በሕግ ላይ የተመሠረተውን የራሴን ጽድቅ ትቼ በእምነት ላይ የተመሠረተውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ በክርስቶስ በማመን ለማግኘትና ከእርሱም ጋር ለመሆን ነው።


ገና በዐይን ስለማይታዩት ነገሮች እግዚአብሔር ባስጠነቀቀው ጊዜ ኖኅ እግዚአብሔርን በመፍራት ቤተሰቡን ለማዳን መርከብን የሠራው በእምነት ነው፤ በኖኅም እምነት ዓለም ኃጢአተኛ መሆኑ ታውቆ ተፈረደበት፤ ኖኅም በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ ወረሰ።


ነገር ግን ሰው የሚጸድቀው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጂ ሕግን በመፈጸም እንዳልሆነ እናውቃለን፤ እኛም ሕግን በመፈጸም ሳይሆን በክርስቶስ በማመን እንድንጸድቅ በኢየሱስ ክርስቶስ አምነናል፤ ማንም ሰው የኦሪትን ሕግ በመፈጸም አይጸድቅም።


አብርሃም ገና ከመገረዙ በፊት እምነቱ ጽድቅ ሆኖ እንደ ተቈጠረለት ማረጋገጫ ምልክት እንዲሆነው ተገረዘ፤ ስለዚህ አብርሃም፥ ሳይገረዙ ለሚያምኑና እምነታቸው ጽድቅ ሆኖ ለሚቈጠርላቸው ሁሉ አባት ነው።


እናንተ ከእስራኤል ማኅበረሰብ ግንኙነት የሌላችሁ፥ ለተስፋው ቃል ኪዳን እንግዶች የሆናችሁ፥ በዚህ ዓለምም አንዳች ተስፋ የሌላችሁ፥ ያለ እግዚአብሔር የምትኖሩ፥ ከክርስቶስም የተለያችሁ እንደ ነበራችሁ አስታውሱ።


እኛ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ የጽድቅን ተስፋ በእምነት እንጠባበቃለን።


ኢሳይያስም፦ “ላልፈለጉኝ ተገኘሁ፤ ‘እግዚአብሔር የት ነው?’ ብለው ላልጠየቁኝም ተገለጥሁ፤” በማለት ደፍሮ ተናግሮአል።


እግዚአብሔር ሰዎችን በእምነት ስለ ማጽደቁ ግን እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፤ “በልብህ ወደ ሰማይ ማን ይወጣል?” አትበል፤ ይህም ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤


እንግዲህ ምን እንላለን? እግዚአብሔር ያዳላል ማለት እንችላለን? እግዚአብሔር ያዳላል ማለትስ ከቶ አንችልም!


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔንና ጽድቅን የምትፈልጉ አድምጡኝ፤ ወደ ተጠረባችሁበት ድንጋይና ወደ ወጣችሁበት ጒድጓድ ተመልከቱ።


አሕዛብ እንደሚያደርጉት በስድነት፥ በፍትወት፥ በስካር፥ ቅጥ ባጣ ፈንጠዝያ፥ ያለ ልክ ጠጥቶ በመጨፈርና አጸያፊ በሆነ የጣዖት አምልኮ ያሳለፋችሁት ዘመን ይበቃል።


የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! አንተ ግን ከዚህ ሁሉ ሽሽ፤ ጽድቅን፥ መንፈሳዊነትን፥ እምነትን፥ ፍቅርን፥ በትዕግሥት መጽናትን፥ ገርነትን ተከታተል።


በዚህ ዐይነት በእምነት እንድንጸድቅ ክርስቶስ እስኪመጣ ሕግ ሞግዚታችን ሆኖ ነበር።


እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንደሚያጸድቅ ቅዱስ መጽሐፍ አስቀድሞ አይቶ “ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ይባረካሉ” በማለት አስቀድሞ ለአብርሃም የምሥራቹን ቃል አብሥሮአል።


ሰው በልቡ ሲያምን ይጸድቃል፤ በአፉም ሲመሰክር ይድናል፤


ነገር ግን ጽድቅ የሚያስገኘውን ሕግ ይከተሉ የነበሩት እስራኤላውያን ሕግን ለመፈጸም ባለመቻላቸው ወደ ጽድቅ አልደረሱም።


እንግዲህ እኛ ጽድቅን ያገኘነው በእምነት ስለ ሆነ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም አለን።


ስለዚህ ነው ለአብርሃም እምነቱ ጽድቅ ሆኖ የተቈጠረለት።


ለአብርሃምና ለዘሩ ዓለምን እንደሚወርስ እግዚአብሔር ተስፋ የሰጠው በእምነት ስላገኘው ጽድቅ ነው እንጂ ሕግን በመፈጸሙ አይደለም።


ታዲያ፥ ዳዊት የተናገረው ይህ በረከት ለተገረዙት ብቻ ነውን? ወይስ ላልተገረዙትም? ላልተገረዙትም ነው፤ “አብርሃም በእግዚአብሔር ስላመነ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት” ብለናል።


ነገር ግን የእኛ ኃጢአት የእግዚአብሔርን ጽድቅ የሚያሳይ ከሆነ እንግዲህ ምን እንላለን? እግዚአብሔር ስለ ኃጢአታችን ቢቀጣን ትክክለኛ ፈራጅ አይደለም ማለት ነውን? እዚህ ላይ የምናገረው እንደ ሰው አስተሳሰብ ነው።


ጽድቅንና ቸርነትን የሚከተል ሰው ሕይወትን፥ ብልጽግናንና ክብርን ያገኛል።


እግዚአብሔር የክፉ ሰዎችን መንገድ ይጠላል፤ ቅን አድራጊዎችን ግን ይወዳል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios