ሮሜ 9:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሸክላ ሠሪ ከአንድ ዐይነት የሸክላ ጭቃ አንዱን ዕቃ ለክብር፥ ሌላውን ለተራ አገልግሎት አድርጎ ለመሥራት ሥልጣን የለውምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሸክላ ሠሪ፣ ከሚሠራው ጭቃ፣ አንዳንዱን ሸክላ ለከበረ፣ ሌሎቹን ደግሞ ለተራ አገልግሎት የማድረግ መብት የለውምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይም ሸክላ ሠሪ ከአንድ ዓይነት ጭቃ አንዱን ዕቃ ለክብር፥ አንዱን ደግሞ ለውርደት ሊሠራ በጭቃ ላይ መብት የለውምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሸክላ ሠሪ ከአንድ ጭቃ ግማሹን ለክብር፥ ግማሹንም ለኀሳር አድርጎ ዕቃን ሊሠራ አይችልምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይም ሸክላ ሠሪ ከአንዱ ጭቃ ክፍል አንዱን ዕቃ ለክብር አንዱንም ለውርደት ሊሠራ በጭቃ ላይ ሥልጣን የለውምን? |
መጥረቢያ እንጨት በሚቈርጥበት በባለቤቱ ላይ መነሣት ይችላልን? መጋዝስ በሚሰነጥቅበት ሰው ላይ መነሣት ይችላልን? እንዲሁም በትር በሚይዘው ሰው ላይ ኀይል አይኖረውም።
ከሠሪው ጋር ለሚከራከር ወዮለት! እርሱ እኮ ከሸክላ ዕቃዎች እንደ አንዱ ነው፤ አንድ የሸክላ ሥራ ሸክላ ሠሪውን “ምንድን ነው የምታደርገው? እጀታውስ የት አለ?” ብሎ ሊጠይቅ ይችላልን?
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ንጉሥ ኢኮንያን ከተጣለ በኋላ ማንም እንደማይፈልገው ሰባራ ገንቦ መሆኑ ነውን? እርሱና ልጆቹ ተማርከው ወደማያውቁት አገር የተወሰዱት ለምንድን ነው?”
ጌታም ሐናንያን እንዲህ አለው፦ “እርሱ ስሜን ለአረማውያን፥ ለነገሥታትና ለእስራኤል ሰዎች የሚያሳውቅ፥ የእኔ ምርጥ መሣሪያ ስለ ሆነ ወደ እርሱ ሂድ፤