ሮሜ 6:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁን እናንተ የምትኖሩት ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላልሆነ ኃጢአት ሊገዛችሁ አይገባም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላልሆናችሁ፣ ኀጢአት አይገዛችሁምና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላልሆናችሁ ኃጢአት አይገዛችሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ኀጢአት አትገዛችሁም፤ የኦሪትን ሕግ ከመሥራት ወጥታችሁ ወደ እግዚአብሔር ጸጋ ገብታችኋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና። |
ስለዚህ ተስፋው የተመሠረተው በእምነት ላይ ነበር፤ ይህም ተስፋ ለአብርሃም ዘሮች ሁሉ ከእግዚአብሔር በጸጋ የተሰጠ መሆኑ በዚህ ተረጋግጦአል። ይህም ሕግን ለሚከተሉት ሰዎች ብቻ ሳይሆን እንደ አብርሃም ላመኑ ሁሉ ነው፤ በዚህም መሠረት አብርሃም የሁላችንም አባት ነውና።
በአንድ ሰው ኃጢአት ምክንያት ሞት በሰው ሁሉ ላይ ሥልጣን ካገኘ የእግዚአብሔርን የተትረፈረፈ ጸጋና ነጻ ስጦታ ተቀብለው የጸደቁ ሁሉ በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት በድል አድራጊነት በሕይወት ይኖራሉ።
እንግዲህ የአንዱ የአዳም ኃጢአት የቅጣትን ፍርድ በሰው ሁሉ ላይ እንዳመጣ እንዲሁም የአንዱ የክርስቶስ የጽድቅ ሥራ ብዙዎችን ከቅጣት ነጻ አድርጎ ሕይወትን ይሰጣል።
ክርስቶስ ከዐመፃ ሁሉ ሊያድነንና መልካም ሥራ ለመሥራት ትጉሆችና ለእርሱ የተለየን ንጹሕ ሕዝብ እንድንሆን ያነጻን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።
“እነሆ፥ ከዚህ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን የሚከተለው ነው ይላል ጌታ፤ እኔ ሕጌን በአእምሮአቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።