ትዕቢተኞችንና ትምክሕተኞችን ከመካከላችሁ ስለማስወግድ በእኔ ላይ ስለ ፈጸማችሁት በደል በዚያን ጊዜ አታፍሩበትም፤ ከእንግዲህ ወዲህ በተቀደሰው ተራራዬ ላይ አትታበዩም።
ሮሜ 3:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ የምንመካበት ነገር ምን አለ? በምንም አንመካም! የማንመካበትስ ምክንያት ምንድን ነው? ሕግን ስለምንፈጽም ነውን? አይደለም፤ ነገር ግን በእምነት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ ትምክሕት ወዴት ነው? እርሱማ ቀርቷል። በየትኛው ሕግ? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፤ በእምነት ሕግ ነው እንጂ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ትምክህት ወዴት ነው? እርሱ ቀርቶአል። በየትኛው ሕግ? በሥራ ነውን? አይደለም፤ ነገር ግን በእምነት ሕግ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትምክሕት ወዴት አለ? እርሱ ቀርቶአል፤ በየትናውስ ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፤ በእምነት ሕግ ነው እንጂ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትምክህት እንግዲህ ወዴት ነው? እርሱ ቀርቶአል። በየትኛው ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፥ በእምነት ሕግ ነው እንጂ። |
ትዕቢተኞችንና ትምክሕተኞችን ከመካከላችሁ ስለማስወግድ በእኔ ላይ ስለ ፈጸማችሁት በደል በዚያን ጊዜ አታፍሩበትም፤ ከእንግዲህ ወዲህ በተቀደሰው ተራራዬ ላይ አትታበዩም።
የሕግ ትእዛዝ የሚመለከተው ከሕግ በታች ያሉትን እንደ ሆነ እናውቃለን፤ በዚህ ምክንያት ሰዎች የሚያመካኙት አጥተው ዝም ይላሉ፤ ዓለሙም ሁሉ በእግዚአብሔር ፍርድ ሥር ይሆናል።
ይሁን እንጂ ከአእምሮዬ ሕግ ጋር እየተቃረነ በሰውነቴ ክፍሎች ውስጥ ለሚሠራው የኃጢአት ሕግ እስረኛ የሚያደርገኝ ሌላ የተፈጥሮ ዝንባሌ በሰውነቴ ክፍሎች ውስጥ መኖሩን አያለሁ።
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለሚያድነኝ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን! እንግዲህ እኔ በአእምሮዬ፥ ለእግዚአብሔር ሕግ ተገዢ ስሆን በሥጋ ባሕርዬ ለኃጢአት ሕግ ተገዢ ሆኜአለሁ።
“ስለምን ወደ ጽድቅ አልደረሱም?” ቢባል እነርሱ ጽድቅን ለማግኘት የፈለጉት በእምነት ሳይሆን በሥራ ስለ ሆነ ነው፤ ስለዚህ በማሰናከያ ድንጋይ ተሰናከሉ፤
አንተ ከሌሎች በምን ትበልጣለህ? ከሌላ ያልተቀበልከውስ ነገር ምን አለ? ታዲያ፥ ሁሉን ነገር የተቀበልከው ከሌላ ከሆነ እንዳልተቀበለ ሰው ስለምን ትመካለህ?
ነገር ግን ሰው የሚጸድቀው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጂ ሕግን በመፈጸም እንዳልሆነ እናውቃለን፤ እኛም ሕግን በመፈጸም ሳይሆን በክርስቶስ በማመን እንድንጸድቅ በኢየሱስ ክርስቶስ አምነናል፤ ማንም ሰው የኦሪትን ሕግ በመፈጸም አይጸድቅም።
ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የተስፋ ቃል ለሚያምኑ እንዲሰጥ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚለው ዓለም በሙሉ ለኃጢአት በመገዛት የኃጢአት እስረኛ ሆኖአል።