ሮሜ 3:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውን የሚጐዳ ክፉ ቃል ለመናገር አፋቸው እንደ መቃብር የተከፈተ ነው፤ በምላሳቸው ያታልላሉ፤ የከንፈራቸውም ንግግር እንደ እባብ መርዝ የሚጐዳ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጕረሯቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።” “በከንፈሮቻቸው የእባብ መርዝ አለ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጉሮሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸውም አታለዋል፤” “የእባብ መርዝ ከከንፈሮቻቸው በታች አለ፤” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጕረሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በአንደበታቸውም ሸነገሉ፤ ከከንፈሮቻቸውም በታች የእባብ መርዝ አለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጕሮሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፥ በመላሳቸውም ሸንግለዋል፤ የእባብ መርዝ ከከንፈሮቻቸው በታች አለ፤ |
ጠላቶቼ የሚናገሩት ሁሉ ከእውነት የራቀ ስለ ሆነ፥ ከአፋቸው እውነት አይገኝም፤ ሐሳባቸውም በተንኰል የተሞላ ነው፤ ጒሮሮአቸውም እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸውም ሰውን ይሸነግላሉ።
ከቶ አያስቀርም! “ከቃልህ የተነሣ እውነተኛ ትሆናለህ፤ ባላጋራህንም በፍርድ ትረታለህ” ተብሎ እንደ ተጻፈው ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ቢሆንም እግዚአብሔር እውነተኛ ነው።