እኔ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁን መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁ በጎ አድርጉ፤ ክፉ ለሚያደርጉባችሁና ለሚያሳድዱአችሁ ጸልዩ” እላችኋለሁ።
ሮሜ 12:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚያሳድዱአችሁንም መርቁ፤ መርቁአቸው እንጂ አትርገሙአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያሳድዷችሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አትርገሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አትርገሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አትርገሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፥ መርቁ እንጂ አትርገሙ። |
እኔ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁን መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁ በጎ አድርጉ፤ ክፉ ለሚያደርጉባችሁና ለሚያሳድዱአችሁ ጸልዩ” እላችኋለሁ።
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ፦ “አባት ሆይ! የሚያደርጉትን ስለማያውቁ ይቅር በላቸው!” አለ። ወታደሮቹም ዕጣ ተጣጥለው የኢየሱስን ልብስ ተከፋፈሉ።
ማንም ሰው በክፉ ፋንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ይልቅስ ሁልጊዜ እናንተ ለእርስ በርሳችሁም ሆነ እንዲሁም ለሌሎች ሰዎች ሁሉ መልካም ለማድረግ ትጉ።