ራእይ 9:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈረሶቹንና በፈረሶቹ ላይ የተቀመጡትን ሰዎች በራእይ ያየኋቸው እንደሚከተለው ነበር፦ በደረታቸው ላይ የነበረው ጥሩር እንደ እሳት ፍም ቀይ፥ እንደ ያክንት ጥቊር ሰማያዊ፥ እንደ ዲን ቢጫ ይመስል ነበር፤ የፈረሶቹም ራስ የአንበሳ ራስ ይመስል ነበር፤ ከአፋቸው እሳትና ጢስ ዲንም ይወጣ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በራእዬ ያየኋቸው ፈረሶችና በላያቸውም የተቀመጡት ይህን ይመስሉ ነበር፤ ጥሩራቸው እንደ እሳት ቀይ፣ እንደ ያክንት ሰማያዊና እንደ ዲን ብጫ ነበር፤ የፈረሶቹ ራስ የአንበሶችን ራስ ይመስል ነበር። ከአፋቸውም እሳትና ጢስ፣ ዲንም ይወጣ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈረሶቹንና በእነርሱም ላይ የተቀመጡትን እንዲሁ በራእይ አየሁ፤ እሳትና ያክንት ዲንም የሚመስል ጥሩር ነበራቸው፤ የፈረሶቹም ራስ እንደ አንበሳ ራስ ነበረ፤ ከአፋቸውም እሳትና ጢስ ዲንም ወጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈረሶቹንና በእነርሱም ላይ የተቀመጡትን እንዲሁ በራእይ አየሁ፤ እሳትና ያክንት ዲንም የሚመስል ጥሩር ነበራቸው፤ የፈረሶቹም ራስ እንደ አንበሳ ራስ ነበረ፤ ከአፋቸውም እሳትና ጢስ ዲንም ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈረሶቹንና በእነርሱም ላይ የተቀመጡትን እንዲሁ በራእይ አየሁ፤ እሳትና ያክንት ዲንም የሚመስል ጥሩር ነበራቸው፤ የፈረሶቹም ራስ እንደ አንበሳ ራስ ነበረ፥ ከአፋቸውም እሳትና ጢስ ዲንም ወጣ። |
ዳዊት በበረሓ በሚገኘው ምሽግ ውስጥ ሳለ ከጋድ ነገድ መጥተው ከእርሱ ሠራዊት ጋር የተባበሩት ዝነኞችና የጦር ልምድ ያላቸው ወታደሮች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፤ እነርሱ ጋሻና ጦር ይዘው በመዋጋት የታወቁ ነበሩ፤ አስፈሪነታቸው እንደ አንበሳ ሲሆን ፈጣንነታቸው በተራራ ላይ እንደሚዘል ሚዳቋ ነበር፤
ከብዙ ዘመናት በፊት የአሦር ንጉሠ ነገሥት የሚቃጠልበት ቦታ ተዘጋጅቶ ነበር፤ ያም ቦታ ሰፊና ጥልቅ ሆኖ ብዙ እንጨት ተከማችቶበት ነበር፤ እንደ ዲን ጅረት የሚፈሰው የእግዚአብሔር እስትንፋስ እሳቱን ያቀጣጥለዋል።
አምልጦ የመጣው ሰው እኔ ዘንድ ከመድረሱ ከአንድ ቀን በፊት በምሽቱ የእግዚአብሔር ኀይል ወደ እኔ መጣ፤ በማግስቱ ጠዋት ሰውዬው ወደ እኔ ከመምጣቱ በፊት እግዚአብሔር አንደበቴን ከፈተልኝ፤ ስለዚህ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መናገር አልተሳነኝም።
በዚህም ጸሎት ላይ ሳለሁ በመጀመሪያው ራእይ ያየሁት ገብርኤል እኔ ወዳለሁበት ስፍራ በፍጥነት እየበረረ መጣ፤ ጊዜውም የሠርክ መሥዋዕት የሚቀርብበት ወቅት ነበር።
የእግዚአብሔርን የቊጣ የወይን ጠጅ ይጠጣሉ፤ ይህም የወይን ጠጅ ሳይበረዝ በቊጣው ጽዋ የተቀዳ ነው፤ እንዲሁም በቅዱሳን መላእክት ፊትና በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሠቃያሉ፤
ነገር ግን አውሬው ተያዘ፤ ከእርሱም ጋር በፊቱ ብዙ ተአምራት ያደርግ የነበረው ሐሰተኛው ነቢይ ተያዘ፤ እርሱ የአውሬው ምልክት የነበረባቸውንና ለአውሬውም ምስል ይሰግዱ የነበሩትን ተአምራት እያደረገ ያስታቸው ነበር፤ እነዚህ ሁለቱ በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር ከነሕይወታቸው ተጣሉ።
ያሳታቸው ዲያብሎስ፥ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት በዲን በሚቃጠል እሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ፤ በዚያም ሌሊትና ቀን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሠቃያሉ።
አምስተኛው ሰርዶንክስ፥ ስድስተኛው ሰርድዮን፥ ሰባተኛው ክርስቲሎቤ፥ ስምንተኛው ቢረሌ፥ ዘጠነኛው ወራውሬ፤ ዐሥረኛው ክርስጵራስስ፥ ዐሥራ አንደኛው ያክንት፥ ዐሥራ ሁለተኛው አሜቴስጢኖስ ነበረ።
ነገር ግን ፈሪዎች፥ እምነተ ቢሶች፥ ርኩሶች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ አመንዝሮች፥ አስማተኞች፥ ጣዖት አምላኪዎች፥ ውሸታሞች ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲን በሚቃጠለው በእሳት ባሕር ውስጥ ይሆናል፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”
የብረት ጥሩር የሚመስል ጥሩር ነበራቸው፤ የክንፎቻቸው ድምፅ ወደ ጦርነት የሚጋልቡ ብዙ ፈረሶችና ሠረገላዎች የሚያሰሙትን ድምፅ ይመስል ነበር።