ራእይ 22:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም እንዲህ አለኝ፤ “ጊዜው የቀረበ ስለ ሆነ የዚህን መጽሐፍ የትንቢት ቃል በማኅተም አትዝጋው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አለኝ፤ “ጊዜው ስለ ደረሰ፣ የዚህን መጽሐፍ የትንቢት ቃል በማኅተም አትዝጋው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሀም አለኝ፦ “ዘመኑ ቀርቦአልና የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል በማኅተም አትዝጋው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእኔም “ዘመኑ ቀርቦአልና የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል በማኅተም አትዝጋው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእኔም፦ ዘመኑ ቀርቦአልና የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል በማኅተም አትዝጋው። |
እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለዚህ ጉዳይ የምለውን ንገራቸው፤ ይህ ምሳሌ እዚሁ ላይ እንዲያበቃ አደርገዋለሁ፤ ዳግመኛም በእስራኤል አይነገርም፤ በዚህ ፈንታ ‘እነሆ ጊዜው ደርሶአል፤ የትንቢቱም ቃል ሁሉ ሊፈጸም ነው!’ ብለህ ንገራቸው።
እንደገናም እንዲህ አለኝ፦ “ዳንኤል ሆይ! የዓለም መጨረሻ እስከሚሆንበት ጊዜ ድረስ መጽሐፉን ዘግተህ አሽገው፤ የትንቢቱንም ቃል በምሥጢር ያዝ፤ በዚያን ጊዜ ሰዎች ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ይራወጣሉ፤ ምርምርና ዕውቀትም ይበዛል።”
እርሱም እንዲህ ሲል መለሰልኝ፦ “ዳንኤል ሆይ! የዓለም መጨረሻ እስከሚሆንበት ጊዜ ድረስ ቃሉ የትንቢቱም ቃል ምሥጢር ሆኖ ስለሚጠበቅ እንግዲህ አንተ ሂድ።
ስለ ጠዋትና ስለ ማታ መሥዋዕት የተነገረው ራእይ እውነት ነው፤ አንተ ግን ይህ ራእይ የሚፈጸምበት ጊዜ ሩቅ ስለ ሆነ በምሥጢር ያዘው” አለኝ።
እንግዲህ ከእንቅልፍ የምትነቁበት ሰዓት አሁን መድረሱን ዕወቁ፤ በፊት ካመንበት ጊዜ ይልቅ አሁን የምንድንበት ቀን ይበልጥ ወደ እኛ ቀርቦአል።
“የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያን፥ ማለትም ወደ ኤፌሶን፥ ወደ ሰምርኔስ፥ ወደ ጴርጋሞን፥ ወደ ትያጥሮን፥ ወደ ሰርዴስ፥ ወደ ፊላደልፍያና ወደ ሎዶቅያ ላክ።”
ይህ ሁሉ የሚፈጸምበት ጊዜ ቅርብ ስለ ሆነ ይህን የትንቢት ቃል የሚያነብ የተባረከ ነው! እንዲሁም የትንቢቱን ቃል የሚሰሙና በትንቢቱም ውስጥ የተጻፈውን የሚፈጽሙ የተባረኩ ናቸው።
ሰባቱ ነጐድጓዶች ድምፃቸውን ባሰሙ ጊዜ እኔ ልጽፍ አሰብኩ፤ ነገር ግን “ሰባቱ ነጐድጓዶች የተናገሩትን አሽገህ በምሥጢር ያዘው እንጂ አትጻፈው!” የሚል ድምፅ ከሰማይ ሰማሁ።
“እኔ ኢየሱስ ይህን ምስክርነት እንዲሰጣችሁ መልአኬን ለአብያተ ክርስቲያን ልኬአለሁ፤ እኔ የዳዊት የትውልድ ሐረግና ዘር ነኝ፤ የሚያበራ የንጋት ኮከብ ነኝ።”
እነሆ፥ በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን የትንቢት ቃል የሚሰማውን ሁሉ አስጠነቅቃለሁ፤ ማንም በዚህ ቃል ላይ አንዳች ነገር ቢጨምር፥ በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች እግዚአብሔር ይጨምርበታል።
መልአኩ ግን “ተው ይህን አታድርግ! እኔ ከአንተና ከወንድሞችህ ከነቢያት ጋር የዚህን መጽሐፍ ቃል ከሚፈጽሙ ሰዎች ጋር አገልጋይ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ!” አለኝ።