ራእይ 18:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰማይ ሆይ! በእርስዋ ደስ ይበልህ! እግዚአብሔር ስለ እናንተ በእርስዋ ላይ ስለ ፈረደባት እናንተ ቅዱሳንና ሐዋርያት ነቢያትም ደስ ይበላችሁ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሰማይ ሆይ፤ በርሷ ላይ ሐሤት አድርግ! ቅዱሳን፣ ሐዋርያትና ነቢያትም ሐሤት አድርጉ! በእናንተ ላይ ባደረሰችው ነገር እግዚአብሔር ፈርዶባታልና።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሰማይ ሆይ! ቅዱሳን፥ ሐዋርያትና ነቢያት ሆይ! ስለተፈረደባት በእርሷ ላይ ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሰማይ ሆይ! ቅዱሳን ሐዋርያት ነቢያትም ሆይ! በእርስዋ ላይ ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰማይ ሆይ፥ ቅዱሳን ሐዋርያት ነቢያትም ሆይ፥ በእርስዋ ላይ ደስ ይበላችሁ፥ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና። |
በምድር ላይ የሚኖሩትን ሕዝቦች ስለ ኃጢአታቸው ለመቅጣት እግዚአብሔር ከሰማይ መኖሪያው ይገለጣል፤ በዚያን ጊዜ በምድር ላይ ተሸሽገው የሚኖሩ የነፍሰ ገዳዮች ሥራ ይጋለጣል፤ ምድርም በላይዋ የፈሰሰውን ደም ታጋልጣለች። የተገደሉትንም አትደብቅም።
ሰማያት ሆይ! እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን በማዳን ክብሩን ገልጦአልና በደስታ ዘምሩ፤ ምድርም ከታች እልል በዪ፤ ተራራዎች፥ ጫካዎችና በውስጣቸው የምትገኙ ዛፎች ሁሉ የደስታ ድምፅ እያሰማችሁ ፈንድቁ።
እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ያስተላለፈውን የቅጣት ፍርድ አንሥቶላችኋል፤ ጠላቶቻችሁንም አስወግዶላችኋል፤ የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ነው፤ ከእንግዲህ ወዲህ ጥፋት ይደርስብናል ብላችሁ አትፈሩም።
ይህም ምሥጢር በእግዚአብሔር መንፈስ ለቅዱሳን ሐዋርያቱና ነቢያቱ አሁን እንደተገለጠው ዐይነት ባለፉት ዘመናት ለነበሩት ሰዎች አልተገለጠም።
እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ አንዳንዶቹ ነቢያት፥ አንዳንዶቹ የወንጌል ሰባኪዎች፥ አንዳንዶቹ የምእመናን እረኞች፥ አንዳንዶቹ አስተማሪዎች እንዲሆኑ ስጦታዎችን ሰጣቸው።
ከዚህ በፊት ቅዱሳን ነቢያት የተናገሩትን ቃልና በእናንተ ሐዋርያት አማካይነት ያገኛችሁትን የጌታችንንና የአዳኛችንን ትእዛዝ እንድታስታውሱ እፈልጋለሁ።
ስለዚህ ሰማያትና በውስጣቸው የምትኖሩ ሁሉ ደስ ይበላችሁ! ጥቂት ጊዜ ብቻ እንደ ቀረው ስላወቀ ዲያብሎስ በታላቅ ቊጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና ምድርና ባሕር ወዮላችሁ!”
በሰጠችው መጠን ስጥዋት፤ ባደረገችውም ሥራ እጥፍ ክፈልዋት፤ እርስዋ ልዩ ልዩ መጠጦችን በቀላቀለችበት ጽዋ ውስጥ እጥፍ ኀይለኛ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት፤
እነርሱ በታላቅ ድምፅ “ቅዱስና እውነተኛ፥ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ፥ በምድር ባሉት ሰዎች ላይ የማትፈርደውና ስለ ደማችንም የማትበቀለው እስከ መቼ ነው!” እያሉ ጮኹ።
እግዚአብሔር ሆይ! ጠላቶችህን ሁሉ በዚህ ዐይነት አጥፋ፤ ወዳጆችህ ግን እንደ ንጋት ፀሐይ ይድመቁ። ከዚህ በኋላ በምድሪቱ ላይ አርባ ዓመት ሙሉ ሰላም ሆነ።