የእግዚአብሔር ድምፅ አጋዘንን እንድትወልድ ያደርጋል የዛፎችን ቅጠል ያረግፋል፤ በመቅደሱም ያሉ ድምፁን ሲሰሙ “ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!” ይላሉ።
ራእይ 15:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቤተ መቅደሱም ከእግዚአብሔር ክብርና ኀይል የተነሣ በጢስ ተሞላ፤ ሰባቱ መላእክት የያዙአቸው ሰባት መቅሠፍቶች እስከ ተፈጸሙ ድረስ ማንም ወደ ቤተ መቅደሱ መግባት አልቻለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤተ መቅደሱም ከእግዚአብሔር ክብር፣ ከኀይሉም በወጣው ጢስ ተሞላ፤ የሰባቱ መላእክት ሰባት መቅሠፍቶች እስኪፈጸሙ ድረስ ማንም ወደ ቤተ መቅደሱ መግባት አልቻለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤተ መቅደሱ ከእግዚአብሔር ክብርና ከኀይሉ የተነሣ በጢስ ተሞላ፤ የሰባቱ መላእክት ሰባቱ መቅሰፍት እስኪፈጸሙ ድረስ ማንም ወደ መቅደሱ መግባት አልቻለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእግዚአብሔርም ክብርና ከኀይሉ ጢስ በመቅደሱ ሞላበት፤ የሰባቱ መላእክት ሰባቱ መቅሰፍት እስኪፈጸሙ ድረስ አንድ እንኳ ወደ መቅደሱ ይገባ ዘንድ አልቻለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእግዚአብሔርም ክብርና ከኃይሉ ጢስ በመቅደሱ ሞላበት፥ የሰባቱ መላእክት ሰባቱ መቅሰፍት እስኪፈጸሙ ድረስ አንድ እንኳ ወደ መቅደሱ ይገባ ዘንድ አልቻለም። |
የእግዚአብሔር ድምፅ አጋዘንን እንድትወልድ ያደርጋል የዛፎችን ቅጠል ያረግፋል፤ በመቅደሱም ያሉ ድምፁን ሲሰሙ “ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!” ይላሉ።
እግዚአብሔር በእሳት ስለ ወረደበት መላው የሲና ተራራ በጢስ ተሞላ። ጢሱም ከእሳት ምድጃ እንደሚወጣ ዐይነት ሆኖ ወደ አየር ተትጐለጐለ፤ ሰዎቹም እጅግ ፈርተው ተንቀጠቀጡ።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ሙሴና ሳሙኤል እንኳ በፊቴ ቆመው ቢማልዱ ለዚህ ሕዝብ ምሕረት አላደርግም፤ ስለዚህ ከፊቴ ወዲያ እንዲሄዱ አድርግ።
“እኔ በታቦቱ ስርየት መክደኛ በደመና የምገለጥበት ስለ ሆነ፥ መጋረጃውን አልፎ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት ያለበት ሁልጊዜ ሳይሆን፥ በአንድ በተወሰነ ቀን ብቻ መሆኑን፥ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው፤ ይህን ትእዛዝ የማይፈጽም ከሆነ ይሞታል፤
ሌላም ታላቅና ድንቅ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ የእግዚአብሔር ቊጣ የሚፈጸምባቸውን የመጨረሻ የሆኑትን ሰባት መቅሠፍቶች የያዙትን ሰባት መላእክት አየሁ።