ራእይ 10:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም ትንሽቱን የብራና ጥቅል መጽሐፍ ከመልአኩ እጅ ወስጄ በላኋት፤ በአፌም እንደ ማር. ጣፈጠች፤ ከበላኋት በኋላ ግን ሆዴ መራራ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትንሿንም መጽሐፍ ከመልአኩ እጅ ተቀብዬ በላኋት፤ በአፌ እንደ ማር ጣፈጠች፤ ከበላኋት በኋላ ግን ሆዴ መራራ ሆነ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመልአኩም እጅ ታናሺቱን መጽሐፍ ወስጄ በላኋት፤ በአፌም እንደ ማር ጣፋጭ ሆነች፤ ከበላኋት በኋላም ሆዴ መራራ ሆነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመልአኩም እጅ ታናሺቱን መጽሐፍ ወስጄ በላኋት፤ በአፌም እንደ ማር ጣፋጭ ሆነች፤ ከበላኋት በኋላም ሆዴ መራራ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመልአኩም እጅ ታናሺቱን መጽሐፍ ወስጄ በላኋት በአፌም እንደ ማር ጣፋጭ ሆነች፤ ከበላኋት በኋላም ሆዴ መራራ ሆነ። |
ያም እጅ የብራናውን ጥቅል ፈቶ በፊቴ ዘረጋው፤ እርሱም በሁለት በኩል ጽሑፍ ያለበት መሆኑን አየሁ፤ በእርሱም ላይ የለቅሶ፥ የሐዘንና የዋይታ ቃሎች ተጽፈውበት ነበር።
“የሰው ልጅ ሆይ! ይህን የሰጠሁህን የብራና ጥቅል ብላው! ሆድህንም በእርሱ ሙላው!” አለኝ፤ እኔም በበላሁት ጊዜ ጣፋጭነቱ እንደ ማር. ነበር።
ከዚህ በኋላ “ስለ ብዙ ወገኖች፥ ሕዝቦች፥ ልዩ ልዩ ቋንቋ ስለሚናገሩ ሰዎችና ስለ ነገሥታት እንደ ገና ትንቢት መናገር አለብህ” ተብሎ ተነገረኝ።
ወደ መልአኩም ሄጄ “ትንሽቱን የብራና ጥቅል መጽሐፍ ስጠኝ” አልኩት፤ እርሱም “ውሰድና ብላት፤ በሆድህ መራራ ትሆናለች፤ በአፍህ ግን እንደ ማር. ትጣፍጣለች” አለኝ።