ከዚህ በኋላ ዳዊት ሕዝቡን “አምላካችሁን እግዚአብሔርን አመስግኑ!” አለ፤ መላው ጉባኤም የቀድሞ አባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ወደ መሬት ለጥ ብለውም ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤ ለንጉሡም ክብር ሰጡ።
መዝሙር 96:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ አመስግኑትም! የአዳኝነቱን መልካም ዜና በየቀኑ አብሥሩ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ስሙንም ባርኩ፤ ማዳኑንም ነጋ ጠባ አውሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታ ዘምሩ ስሙንም ባርኩ፥ ዕለት ዕለትም ማዳኑን አውሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደመናና ጭጋግም በዙሪያው ናቸው፤ ፍትሕና ርትዕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው፤ |
ከዚህ በኋላ ዳዊት ሕዝቡን “አምላካችሁን እግዚአብሔርን አመስግኑ!” አለ፤ መላው ጉባኤም የቀድሞ አባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ወደ መሬት ለጥ ብለውም ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤ ለንጉሡም ክብር ሰጡ።
ደግነትህን በልቤ ውስጥ አልደብቅም፤ ስለ ታማኝነትህና ስለ አዳኝነትህ ተናግሬአለሁ፤ ከትልቁ ጉባኤ ዘለዓለማዊ ፍቅርህንና እውነተኛነትህን አልሰውርም።
ለጽዮን መልካም ነገርን የምታበሥሩ ሆይ! ወደ ከፍተኛ ተራራ ውጡ! እናንተ ለኢየሩሳሌም መልካም ዜናን የምታበሥሩ ሆይ! ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ! ጮክ በሉ አትፍሩ! ለይሁዳ ከተሞች፥ “እነሆ፥ አምላካችሁ” በሉ።
በሰማይና በምድር፥ ከምድር በታችና በባሕር፥ በውስጣቸውም ፍጥረቶች ሁሉ “በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ለበጉም ምስጋና፥ ገናናነት፥ ክብርና ኀይል ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሁን!” ሲሉ ሰማሁ።