በደል ያልሠሩትን ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር ታጠፋለህ ብዬ አላስብም፤ ይህንን እንደማታደርገው አምናለሁ፤ ይህንንማ ካደረግህ ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር መቀጣታቸው ነው፤ ይህ ከቶ አይሆንም! የዓለም ሁሉ ፈራጅ በትክክል መፍረድ ይገባው የለምን?”
መዝሙር 94:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ የዓለም ፈራጅ ነህ፤ ስለዚህ ተነሥ፤ ለትዕቢተኞች የሚገባቸውን ቅጣት ስጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ የምድር ዳኛ ሆይ፤ ተነሥ፤ ለትዕቢተኞች የእጃቸውን ስጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምድር ፈራጅ ሆይ፥ ተነሥ፥ ለትዕቢተኞች ፍዳቸውን ክፈላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእምነት ወደ ፊቱ እንድረስ፥ በዝማሬም ለእርሱ እልል እንበል፤ |
በደል ያልሠሩትን ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር ታጠፋለህ ብዬ አላስብም፤ ይህንን እንደማታደርገው አምናለሁ፤ ይህንንማ ካደረግህ ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር መቀጣታቸው ነው፤ ይህ ከቶ አይሆንም! የዓለም ሁሉ ፈራጅ በትክክል መፍረድ ይገባው የለምን?”
አምላካችን ሆይ! በእኛ ላይ አደጋ ሊጥሉ በብዛት የመጡትን እነዚህን ሠራዊት ሁሉ መቋቋም ስለማንችል አንተ ራስህ ፍረድባቸው፤ የአንተን ርዳታ ለማግኘት ዐይናችንን ወደ አንተ ከማንሣት በቀር ሌላ ምንም ማድረግ እንደሚገባን አናውቅም።”
ነገር ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “በኢየሩሳሌምና በጽዮን ተራራ የማደርገውን ሁሉ ከፈጸምኩ በኋላ ስለ ትምክሕቱና ስለ ትዕቢቱ ሁሉ ብዛት የአሦርንም ንጉሠ ነገሥት ደግሞ እቀጣለሁ።”
የሰዎች ኲራት ይጠፋል፤ እብሪት የሞላበት ትዕቢታቸውም ያከትማል፤ ጣዖቶች ሁሉ ይደመሰሳሉ፤ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ብቻ በክብር ከፍ ከፍ ይላል።
ዐይንህን በትዕቢት አቅንተህ፥ ድምፅህን ከፍ አድርገህ በመጮኽ የተዳፈርከውና የተሳደብከው ማንን ይመስልሃል? የእስራኤልን ቅዱስ አይደለምን?’
በእኔ ላይ ስለ መቈጣትህና ስለ ልብህ ትዕቢት ሁሉ ሰምቼአለሁ፤ ስለዚህ አሁን በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህም ልጓም አግብቼ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።”
“እነሆ፥ እኔ ናቡከደነፆር ለሰማይ ንጉሥ ምስጋና፥ ክብርና ውዳሴ አቀርባለሁ፤ እርሱ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ነው፤ መንገዱም ፍትሓዊ ነው፤ በትዕቢት የሚመሩትንም ሁሉ ማዋረድ ይችላል።”
እያንዳንዱ በምድራዊ ሕይወቱ ላደረገው ክፉም ሆነ ደግ ነገር እንደየሥራው ዋጋውን ለመቀበል ሁላችንም በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት መቅረብ አለብን።
እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ታዘዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።