ወደ እኔ ተመልሰህ ራራልኝ፤ ለእኔ ለአገልጋይህ ብርታትን ስጠኝ፤ እኔን የሴት አገልጋይህን ልጅ አድነኝ።
ወደ እኔ ተመልከት፤ ማረኝም፤ ለባሪያህ ኀይልህን ስጥ፤ የሴት ባሪያህንም ልጅ አድን።
ወደ እኔ ተመልከት፥ ራራልኝ፥ ኃይልህን ለአገልጋይህ፥ ማዳንህንም ለአግልጋይቱ ልጅ ለእኔ ስጥ።
እግዚአብሔር ሆይ! እኔ የአንተ ነኝ፤ የብላቴናይቱ አገልጋይህ ልጅ ነኝ፤ እስራቴን ፈተህልኛል። ከሞት ያዳንከኝ አንተ ነህ።
ወደ እኔ ተመለስ፤ ለሚወዱህ ሁሉ እንደምታደርገውም ምሕረት አድርግልኝ።
እኔ የአንተ ስለ ሆንኩ አድነኝ! ትእዛዞችህንም ለማክበር እፈልጋለሁ።
በጠራሁህ ጊዜ ሰማኸኝ፤ በብርታትህም አበረታኸኝ።
እኔ ብቸኛና ችግረኛ ስለ ሆንኩ አምላክ ሆይ! ወደ እኔ ተመለስ፤ በጎነትንም አድርግልኝ።
ጠላቶቼ ብዙ ክፉ ነገር በእኔ ላይ በመናገር “መቼ ይሞታል? መቼስ ስሙ ተረስቶ ይቀራል?” ይላሉ።
እግዚአብሔር ሆይ! ቸርነት በተሞላበት ፍቅርህ ጸሎቴን ስማ፤ በታላቁ ምሕረትህ ወደ እኔ ተመለስ።
ወደ ጽዮን ተራራ መንፈሳዊ ጒዞ ለማድረግ የሚፈልጉና የአንተን ርዳታ የሚያገኙ እንዴት የተባረኩ ናቸው?
እግዚአብሔር ሆይ! ቊጣህ እስከ መቼ ይቈያል? እባክህ ለአገልጋዮችህ ራራ!
“ ‘ጽድቅና ኀይል የሚገኘው ከእግዚአብሔር ብቻ ነው’ ብለው ስለ እኔ ይናገራሉ፤ የሚጠሉኝ ሁሉ ወደ እኔ መጥተው በዕፍረት ላይ ይወድቃሉ።
እኔ አምላካቸው አበረታቸዋለሁ እነርሱም ለቃሌ ይታዘዛሉ።” እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
ከዚያም በኋላ ማርያም፥ “እነሆ! እኔ የጌታ አገልጋይ ነኝ፤ አንተ እንዳልክ ይሁንልኝ” አለችው። በዚህ ጊዜ መልአኩ ተለይቶአት ሄደ።
እግዚአብሔር ውስጣዊውን ሰውነታችሁን የሚያጠነክር ኀይል በመንፈሱ አማካይነት ከክብሩ ባለጸግነት እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ።
በቀረውስ በጌታና በእርሱም ታላቅ ኀይል በርቱ፤
ኀይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን ነገር ማድረግ እችላለሁ።
ጌታ በገናናው ኀይሉ ብርታቱን ሁሉ ይስጣችሁ፤ በትዕግሥትም ሁሉን ነገር ለመቻል በደስታ የተዘጋጃችሁ ለመሆን ያብቃችሁ፤