ለእኔ የምታሳየው ዘለዓለማዊው ፍቅርህ እንዴት ታላቅ ነው! ወደ ሲኦል ጥልቀት ከመውረድ አዳንከኝ።
ለእኔ ያሳየሃት ምሕረት ታላቅ ናትና፤ ነፍሴንም ከሲኦል ጥልቀት አውጥተሃል።
ጽኑ ፍቅርህ በእኔ ላይ ታላቅ ናትና፥ ነፍሴንም ከታችኛይቱ ሲኦል አድነሃታልና።
ሕይወታቸውንም ከጥፋት ይጠብቃል፤ ከሞት መቅሠፍትም ይታደጋቸዋል።
ሕይወቱ አልፎ ነፍሱ ወደ ሙታን ዓለም ለመውረድ ተቃርባለች።
መልአኩም አዝኖለት ‘ቤዛ ያገኘሁለት ስለ ሆነ፥ ወደ መቃብር እንዳይወርድ፥ ተወው!’ ብሎ ሞትን ያዘዋል።
ወደ ሙታን ዓለም ከመውረድም አዳነኝ፤ እነሆ፥ አሁን በሕይወት ተገኝቼ ብርሃንን አያለሁ።’
ዘለዓለማዊው ፍቅርህ ከሰማያት በላይ ነው፤ ታማኝነትህም ወደ ጠፈር ይደርሳል።
እግዚአብሔር ከሞት አዳነኝ፤ እንባዬ እንዲቆም አደረገ፤ እግሮቼንም ከመደናቀፍ ጠበቃቸው።
ነፍሴን በሲኦል አትተዋትም፤ ታማኝህንም መበስበስ እንዲደርስበት አታደርግም።
እግዚአብሔር ሆይ! ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፤ ወደ ጥልቁም ከመውረድ ሕይወቴን ጠበቅኸው።
ለእርሱ ታማኞች አገልጋዮች የሆናችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን በዝማሬ አመስግኑት! ለቅዱስ ስሙም ምስጋና አቅርቡለት!
አንተ ከሞት አድነኸኛል፤ ተሰናክዬ እንዳልወድቅም ረድተኸኛል፤ ስለዚህ በሕያዋን ላይ በሚያበራው ብርሃን በእግዚአብሔር ፊት እመላለሳለሁ።
ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ከሰማያት በላይ ነው፤ ታማኝነትህም ወደ ጠፈር ይደርሳል።
አንተ ወደ መቃብር አዘቅት ወደ ጨለመውና ጥልቅ ወደ ሆነው ጒድጓድ አወረድከኝ።
ችግር የደረሰብኝ በእርግጥ ለደኅንነቴ ነው፤ ከአደጋም ሁሉ ሕይወቴን ታድናለህ፤ ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር ትላለህ።
ጐረቤቶችዋና ዘመዶችዋ ሁሉ ጌታ ታላቅ ምሕረቱን እንዳደረገላት ሰምተው ከእርስዋ ጋር ተደሰቱ።
እንዲሁም እግዚአብሔር ከሞት ያስነሣውን፥ ከሚመጣው ቊጣ የሚያድነንን፥ የልጁን የኢየሱስን ከሰማይ መምጣት እንዴት እንደምትጠባበቁም ይመሰክራሉ።