La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 83:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የጌባል፥ የዐሞን፥ የዐማሌቅ፥ የፍልስጥኤምና የጢሮስ ሰዎች ናቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጌባል፣ አሞንና አማሌቅ፣ ፍልስጥኤምም ከጢሮስ ሕዝብ ጋራ ሆነው ዶለቱ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የኤዶማውያን ድንኳኖች እስማኤላውያንም፥ ሞዓብም አጋራውያንም፥

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከኀ​ይል ወደ ኀይ​ልም ይሄ​ዳል፥ የአ​ማ​ል​ክት አም​ላክ በጽ​ዮን ይታ​ያል።

Ver Capítulo



መዝሙር 83:7
7 Referencias Cruzadas  

በንጉሥ ሳኦል ዘመነ መንግሥት የሮቤል ነገድ በሀጋራውያን ላይ አደጋ ጥሎ ሁሉንም በጦርነት ፈጃቸው፤ በገለዓድም ምሥራቃዊ ክፍል ያለውን ርስታቸውን ይዞ የራሱ አደረገ።


ወደ ባሕር መግቢያ በሚወስደው መንገድ ላይ ተቀምጣ ከተለያዩ የጠረፍ ከተሞች ለሚመጡ ነጋዴዎች አገናኝ ለሆነችው ለጢሮስ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገራት፦ ‘ጢሮስ ሆይ! በፍጹም ውብ ነኝ ብለሻል።


የተበላሸውን ለመጠገን በጌባል ልምድ ያካበቱ ባለሙያዎች በአንቺ መካከል ነበሩ፤ መርከበኞች በመርከባቸው ወደ ወደብሽ እየመጡ ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር።’


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የጢሮስ ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ የገቡበትን የወንድምነት ቃል ኪዳን አፍርሰው የማረኳቸውን ሕዝቦች ለኤዶም አሳልፈው ሰጥተዋል፤


የጌባላውያን ምድርና ከምሥራቅ በአርሞንኤም ተራራ ደቡብ ከሚገኘው ከባዓልጋድ ተነሥቶ እስከ ሐማት መተላለፊያ ያለው መላው ሊባኖስ ገና አልተያዘም።


እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ ጊዜ አማሌቃውያን በመንገድ ላይ እየተቃወሙ አስቸግረዋቸው ስለ ነበረ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አማሌቃውያንን ለመቅጣት ወስኖአል።


እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት ወጡ፤ ስለዚህም እስራኤላውያን አቤንዔዜር ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ሰፈሩ፤ ፍልስጥኤማውያንም አፌቅ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ሰፈሩ፤