መዝሙር 76:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ በምድር የተጨቈኑትን ሁሉ ለመቤዠት፥ ለፍርድ በተነሣህ ጊዜ ዓለም ጸጥ አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ ሆይ፤ ይህም የሆነው አንተ የምድር ጐስቋሎችን ለማዳን፣ ለፍርድ በተነሣህ ጊዜ ነው። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍርድን ከሰማይ አሰማህ፥ ምድር ፈራች ዝምም አለች፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ይቅርታን ይረሳልን? በቍጣውስ ምሕረቱን ዘጋውን? |
ነገር ግን በእውነት ለድኾች ይፈርዳል፤ ረዳት ለሌላቸውም ወገኖች ተከላካይ በመሆን መብታቸውን ያስከብራል፤ በበትር እንደሚመታ፥ መረን በተለቀቁት ላይ ይፈርዳል፤ በቃሉም ክፉዎችን ያጠፋል።
እነርሱ እንደ ቅልብ ሰንጋ ወፍረዋል፤ ክፉ ሥራቸውም ገደብ የለሽ ሆኖአል፤ እናትና አባት የሌላቸውን ልጆች መብት አያስከብሩም፤ ለችግረኞችም ትክክለኛ ፍርድ አይፈርዱም።
ትእዛዞቹን የምትፈጽሙ፥ በምድሪቱ የምትኖሩ፥ እናንተ ትሑታን ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፤ የጽድቅን ሥራ ሥሩ፤ በትሕትናም ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤ በዚህም ሁኔታ እግዚአብሔር ቊጣውን በሚገልጥበት ቀን ምናልባት ከቅጣት ታመልጡ ይሆናል።
ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ በከበረና በማይጠፋው ጌጥ በገርነትና በጭምትነት መንፈስ ያጌጠው፥ በልብ ተሰውሮ የሚገኘው፥ ውስጣዊ ሰውነት ይሁን።