መዝሙር 75:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትዕቢተኞችን ‘አትታበዩ’ ክፉዎችን ‘አታምፁ’ እላቸዋለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እብሪተኛውን፣ ‘አትደንፋ’፤ ክፉውንም ‘ቀንድህን ከፍ አታድርግ እለዋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድርና በእርሷ ውስጥ የሚኖሩት ሁሉ ይናወጣሉ፥ እኔም ምሰሶችዋን አጠናሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ በዘለዓለም ተራሮች ሆነህ በድንቅ ታበራለህ። |
“እናንተ ዕውቀት የጐደላችሁ! እስከ መቼ ድረስ የሞኝነትን መንገድ ትከተላላችሁ! እናንተስ ፌዘኞች! እስከ መቼ ድረስ በማፌዝ ትደሰታላችሁ! ሞኞችስ እስከ መቼ ድረስ ዕውቀትን ትጠላላችሁ!
እኔም “እነዚህ ሰዎች የመጡት ምን ሊሠሩ ነው?” ብዬ ጠየቅሁት፤ እርሱም “እነርሱ የመጡት የይሁዳን ምድር ፈጽሞ አጥፍተው፥ ሕዝብዋ ተበታትኖ እንዲቀር ያደረጉትን የአሕዛብ መንግሥታት ለማሸበርና ለመጣል ነው” አለኝ።
እርሱ ድኾችን ከትቢያ ምስኪኖችንም ከዐመድ ላይ ያነሣል፤ ወደ ልዑላንም ደረጃ ከፍ ያደርጋቸዋል፤ የክብርም ዙፋን ያወርሳቸዋል የምድርን መሠረቶች የሠራ እግዚአብሔር ነው፤ በእነርሱም ላይ ዓለምን የፈጠረ እርሱ ነው።