የእግዚአብሔር ሰዎች እንኳ ሳይቀሩ ወደ እነርሱ ያዘነብላሉ፤ የሚነግሩአቸውንም ሁሉ ይቀበላሉ።
ስለዚህ ሕዝቡ ወደ እነርሱ ይነጕዳል፤ ውሃቸውንም በገፍ ይጠጣሉ።
ስለዚህ ሕዝቤም ወደ እነርሱ ይመለሳሉ፥ ከሞላ ውሃቸውም ይጋታሉ፥
አቤቱ፥ ጠላት እስከ መቼ ይሳደባል? ስምህንስ ጠላት ሁልጊዜ ያስቈጣዋል?
እግዚአብሔር የተቀመመ ወይን ጠጅ የተሞላበትን ጽዋ በእጁ ይዞአል፤ በቊጣው ሲያፈስሰው ክፉዎች ሁሉ ይጠጡታል፤ እስከ መጨረሻው ጠብታ ድረስ ይጨልጡታል።