እነሆ፥ እኔ አሁን የሰማንያ ዓመት ሰው ነኝ፤ የሚያስደስቱና የማያስደስቱ ነገሮችን መለየት እችላለሁን? የምበላውንም ሆነ የምጠጣውን ጣዕም መለየት እችላለሁን? ጆሮዬም የወንድና የሴት ዘፋኞችን ድምፅ መስማት ይችላልን? ንጉሥ ሆይ! በጌታዬ ላይ ለምን ተጨማሪ ሸክም እሆንብሃለሁ?
መዝሙር 71:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁንም በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፤ ደካማ በምሆንበትም ጊዜ አትተወኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፤ ጕልበቴም ባለቀበት ጊዜ አትተወኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፥ ጉልበቴም ባለቀ ጊዜ አትተወኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፥ ጠላቶቹም አፈርን ይልሳሉ። |
እነሆ፥ እኔ አሁን የሰማንያ ዓመት ሰው ነኝ፤ የሚያስደስቱና የማያስደስቱ ነገሮችን መለየት እችላለሁን? የምበላውንም ሆነ የምጠጣውን ጣዕም መለየት እችላለሁን? ጆሮዬም የወንድና የሴት ዘፋኞችን ድምፅ መስማት ይችላልን? ንጉሥ ሆይ! በጌታዬ ላይ ለምን ተጨማሪ ሸክም እሆንብሃለሁ?
ዕድሜአችን ሰባ ዓመት ነው፤ ቢበዛም ሰማኒያ ዓመት ነው፤ እነዚያም ዘመናት በችግርና በሐዘን የተሞሉ ናቸው፤ ዕድሜአችን በቶሎ ያልቃል፤ እኛም እናልፋለን።
አርጅታችሁ ጠጒራችሁ እስከሚሸብትበት ጊዜ ድረስ፥ የምጠብቃችሁ እኔ ነኝ፤ ፈጥሬአችኋለሁ፤ እንከባከባችኋለሁም፤ እረዳችኋለሁ፤ ከክፉ ነገርም እጠብቃችኋለሁ።
ይህን መከራ የምቀበለውም በዚህ ምክንያት ነው፤ ነገር ግን ማንን እንዳመንኩ ስለማውቅ አላፍርበትም፤ የተሰጠኝንም ዐደራ እስከዚያ ቀን ድረስ መጠበቅ እንደምችል ተረድቼአለሁ።