መዝሙር 71:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠላቶቼ በእኔ ላይ ክፉ ነገር ይመክራሉ፤ ሊገድሉኝ የሚፈልጉትም በእኔ ላይ ያሤራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠላቶቼ ተነጋግረውብኛልና፣ ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ በአንድ ላይ አሢረዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠላቶቹ በላዬ ተናግረዋልና፥ ነፍሴንም የሚሹአት በአንድነት ተማክረዋልና፥ እንዲህም አሉ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ፤ የሳባና የዓረብ ነገሥታት እጅ መንሻን ያመጣሉ፤ |
ብዙ ሰዎች ፈርተው በሹክሹክታ እንዲህ ሲሉ ሰማሁ፤ “አሁን ኤርምያስን ለመክሰስ መልካም አጋጣሚ ነው!” ወዳጆቼ ናቸው የሚባሉት እንኳ ስሕተት እንዳደርግ ይጠባበቃሉ፤ “ኤርምያስ ሊታለል ይችል ይሆናል፤ ይህም ከሆነ እርሱን ይዘን እንበቀለዋለን፤” ይላሉ።
በዚያኑ ምሽት ሳኦል የዳዊትን ቤት ከበው ማለዳ እንዲገድሉት ሰዎችን ላከ፤ የዳዊት ሚስት ሜልኮል “ዛሬ ማታ ነፍስህን ካላዳንህ በቀር ነገ ጧት ትገደላለህ” ስትል አስጠነቀቀችው፤