እግዚአብሔር ሁልጊዜ በክፉዎች ላይ የሚፈርድ ትክክለኛ ዳኛ ነው።
እግዚአብሔር ጻድቅ ዳኛ ነው፤ ቍጣውንም በየዕለቱ የሚገልጥ አምላክ ነው።
ጋሻዬ በእግዚአብሔር ዘንድ ነው ልበ ቅኖችን የሚያድናቸው።
እግዚአብሔር የእውነት ዳኛ ነው፤ ኀይለኛም ታጋሽም ነው፤ ሁልጊዜም ጥፋትን አያመጣም።
እግዚአብሔር ብቸኛ ዳኛ ስለ ሆነ ሰማያት የእርሱን ፍትሕ ያውጃሉ።
እግዚአብሔር በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል፤ ጌታ ሆይ! እንደ እውነተኛነቴና እንደ ታማኝነቴ ፍረድልኝ።
ፍትሕ እንደገና የዳኝነት መሠረት ትሆናለች፤ ልበ ቅኖችም ሁሉ ይደግፉአታል።
እግዚአብሔር ቀናተኛ ተበቃይ አምላክ ነው፤ በኀይለኛ ቊጣውም፥ በጠላቶቹ ላይ መዓቱን ያወርዳል።
በእርሱ ኀይለኛ ቊጣ ፊት መቆም የሚችል ማን ነው? ቊጣውስ እንደ እሳት በነደደ ጊዜ የሚችለው ማነው? እንደ እሳት የሚያቃጥል ቊጣው በሚወርድበት ጊዜ አለቶች ተሰነጣጥቀው ይበታተናሉ።